አቤቱ፥ የጣልኸን አንተ አይደለህምን? አምላካችን ሆይ፥ ከሠራዊታችን ጋር አትወጣም።
በእግዚአብሔር ቃል ላይ በማመፅ፣ የልዑልን ምክር አቃልለዋልና።
በእግዚአብሔር ቃል ላይ ስለ ዐመፁ፥ የልዑልንም ምክር ስለ ናቁ፥
ይህም ሁሉ የደረሰባቸው በልዑል እግዚአብሔር ትእዛዝ ላይ በማመፃቸውና ምክሩንም በመናቃቸው ነበር።
እግዚአብሔርም ምናሴንና ሕዝቡን ተናገራቸው፤ ግን አልሰሙትም።
እነርሱ ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በሕዝቡ ላይ እስኪወጣ ድረስ፥ ፈውስም እስከማይገኝላቸው ድረስ፥ በእግዚአብሔር መልእክተኞች ይሳለቁ፥ ቃሉንም ያቃልሉ፥ በነቢያቱም ላይ ያፌዙ ነበር።
ይህን የሚጠብቅ ጥበበኛ ማን ነው? እግዚአብሔር ይቅር ባይ እንደ ሆነ ያውቃል።
ወደሚኖሩበትም ሀገር ይሄዱ ዘንድ የቀና መንገድን መራቸው።
ነፍሴን ተመልክተህ ተቤዣት፤ ስለ ጠላቶችም አድነኝ።
አቤቱ፥ የሠራዊት አምላክ፥ የሚሹህ በእኔ አይፈሩ፤ የእስራኤል አምላክ ሆይ፥ ተስፋ የሚያደርጉህ በእኔ አይነወሩ።
“ምክሬን ሁሉ ናቃችሁ፥ ዘለፋዬንም አልተመለከታችሁም፥
“እናይ ዘንድ፥ ሥራውን ያፋጥን፤ እናውቃትም ዘንድ የእስራኤል ቅዱስ ምክር፥ ትምጣ” ለሚሉ ወዮላቸው!
“አንተ በእግዚአብሔር ስም የነገርኸንን ቃል አንሰማም።
ገንዘብን የሚወዱ ፈሪሳውያንም ይህን ሁሉ ነገር ሰምተው ተጠቃቀሱበት።
ፈሪሳውያንና የሕግ ጻፎች ግን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ተቃወሙ፤ በእርሱ አልተጠመቁምና።
ከእግዚአብሔር ምክር ሁሉ የሰወርኋችሁና ያልነገርኋችሁ የለም።
እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱ መጠን እንዲሁ እግዚአብሔር ይህን የማይገባውን ይሠሩ ዘንድ ሰነፍ አእምሮን ሰጣቸው።