መዝሙር 106:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደሚኖሩበትም ሀገር ይሄዱ ዘንድ የቀና መንገድን መራቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አባቶቻችን በግብጽ ሳሉ፣ ታምራትህን አላስተዋሉም፤ የምሕረትህን ብዛት አላሰቡም፤ በባሕሩ አጠገብ፣ ገና ቀይ ባሕር አጠገብ ዐመፁብህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አባቶቻችን በግብጽ ሳሉ ተኣምራትህን አላስተዋሉም፥ የፍቅርህንም ብዛት አላሰቡም፥ በቀይ ባሕር ባለፉ ጊዜ ዐመፁብህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የቀድሞ አባቶቻችን በግብጽ ምድር እርሱ ያደረገውን ድንቅ ነገር ሁሉ አላስተዋሉም፤ ብዙዎቹን የቸርነት ሥራዎቹን አላስታወሱም፤ በቀይ ባሕር አጠገብ ዐመፁ። |
“ይህን ያህል ዘመን የዋሃን ጽድቅን ሲከተሉ አያፍሩም። ሰነፎች፥ እስከ መቼ ድረስ ስሕተትን ትወዳላችሁ? ሰነፎች ስድብን የሚወዱ ናቸው፥ ሰነፎችም ሆነው ዕውቀትን ጠሉ። ለሚዘልፏቸው የተመቹ ሆኑ፤
በስጦታው ሁሉ የእግዚአብሔርን ቸርነትና የእግዚአብሔርን ምስጋና ዐሰብሁ፤ እግዚአብሔር ለእስራኤል ወገኖች እውነተኛ ፈራጅ ነው፤ እንደ ቸርነቱና እንደ ጽድቁ ብዛትም ይቅርታውን ያመጣልናል።
እናንተ አሕዛብ አስቡ፤ ቀድሞ በሥጋ ሥርዐት ነበራችሁ፤ ያልተገዘሩም ይሉአችሁ ነበር፤ እንዲህ የሚሉአችሁም የተገዘሩ ሰዎች ናቸው፤ ግዝረት ግን በሥጋ ላይ የሚደረግ የሰው እጅ ሥራ ነው።
አንተም በግብፅ ምድር ባሪያ እንደ ነበርህ፥ አምላክህም እግዚአብሔር ከዚያ እንዳዳነህ ዐስብ፤ ስለዚህ እኔ ዛሬ ይህን ነገር አዝዝሃለሁ።
እግዚአብሔር ግን ታስተውሉ ዘንድ ልብን፥ ታዩም ዘንድ ዐይንን፥ ትሰሙም ዘንድ ጆሮዎችን እስከ ዛሬ ድረስ አልሰጣችሁም።