ከክፉ ሰዎች ዘንድ ሽሙጥን ገንዘብ አታድርግ፥ በመንገዳቸውም አትቅና።
በክፉ ሰው አትቅና፤ የትኛውንም መንገዱን አትምረጥ።
በግፈኛ ሰው አትቅና፥ መንገዱንም ሁሉ አትምረጥ።
በግፈኞች ሰዎች አትቅና፤ ክፉ ሥራቸውንም አትከተል።
አቤቱ፥ በመዓትህ አትቅሠፈኝ፥ በመቅሠፍትህም አትገሥጸኝ።
ጠላት በቅዱሳንህ ላይ እንደ ከፋ መጠን፥ ሁልጊዜ በትዕቢታቸው ላይ እጅህን አንሣ።
የኃጥኣን ምኞት ክፋት ናት። የጻድቃን ሥር ግን የጸና ነው።
ልብህ በኀጢአተኞች አይቅና፤ ነገር ግን ቀኑን ሙሉ እግዚአብሔርን በመፍራት ኑር፤
ልጄ ሆይ፥ በክፉ ሰዎች አትቅና፥ ከእነርሱም ጋር መኖርን አትውደድ፤
ከፍ ካለው በላይ ከፍ ያለ ይጠብቅሃልና፥ ከእነርሱም በላይ ደግሞ ሌሎች ከፍ ይላሉና በሀገሩ ድሃ ሲበደል፥ ፍርድና ጽድቅም ሲነጠቅ ብታይ በሥራው አታድንቅ።
አስቀድሜ እንደ ነገርኋችሁ ይህን የሚያደርግ የእግዚአብሔርን መንግሥት አያይም።