ምሳሌ 23:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰካራምና አመንዝራ ይደኸያል፥ እንቅልፋምም ሁሉ የተቦጫጨቀ ጨርቅ ይለብሳል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰካራሞችና ሆዳሞች ድኾች ይሆናሉና፤ እንቅልፋምነትም ቡትቶ ያለብሳቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰካራሞችና ሆዳሞች ይደኸያሉና፥ የእንቅልፍም ብዛት የተቦጫጨቀ ጨርቅ ያስለብሳልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰካራሞችና ሆዳሞች ይደኸያሉ፤ ሙያው ማንቀላፋት ብቻ የሆነ ሰውም ደኽይቶ ቡትቶ ለባሽ ይሆናል። |
እናንተ ሰካራሞች፥ ንቁ፤ ለመስከርም ወይንን የምትጠጡ እናንተ ሁላችሁ! ተድላና ደስታ ከአፋችሁ ጠፍትዋልና አልቅሱ፤ እዘኑም።
የሰው ልጅ እየበላና እየጠጣ መጣ፤ እነርሱም ‘እነሆ በላተኛና የወይን ጠጅ ጠጭ፥ የቀራጮችና የኀጢአተኞች ወዳጅ’ ይሉታል። ጥበብም በልጆችዋ ጸደቀች።”
አሁንም ከወንድሞች መካከል ዘማዊ፥ ወይም ገንዘብን የሚመኝ፥ ወይም ጣዖትን የሚያመልክ፥ ወይም ዐመፀኛ፥ ወይም ተራጋሚ፥ ወይም ሰካራም፥ ወይም የሚቀማ ቢኖር እንደዚህ ካለ ሰው ጋር አንድ እንዳትሆኑ ጻፍሁላችሁ፥ እንደዚህ ካለው ሰው ጋር መብልም እንኳ አትብሉ፤
ሌቦች፥ ወይም ቀማኞች፥ ወይም ሰካሮች፥ ወይም ተሳዳቢዎች፥ ወይም ነጣቂዎች፥ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱአትም።
የከተማዉንም ሰዎች፦ ‘ይህ ልጃችን ትዕቢተኛና ዐመፀኛ ነው፥ ቃላችንንም አይሰማም፤ ስስታምና ሰካራም ነው’ ይበሉአቸው።
እነዚህም ፍጻሜያቸው ለጥፋት የሆነ፥ ሆዳቸውን የሚያመልኩ፥ ክብራቸውም ውርደት የሆነባቸው፥ ምድራዊዉንም የሚያስቡ ናቸው።