ወደ ካህኑ ወደ አሮን ልጆች ያመጣዋል፤ ከመልካም ስንዴ ዱቄቱና ከዘይቱም አንድ እፍኝ ሙሉና ነጩንም ዕጣን ሁሉ ወስዶ ካህኑ የእሳት ቍርባን ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ እንዲሆን ለመታሰቢያ በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል።
ዘኍል 5:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ካህኑም ከእህሉ ቍርባን አንድ እፍኝ ሙሉ ለመታሰቢያው ወስዶ በመሠዊያው ላይ ይጨምረዋል። ከዚያም በኋላ ለሴቲቱ ያን ውኃ ያጠጣታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ካህኑ የመታሰቢያ ቍርባን እንዲሆን ዕፍኝ የእህል ቍርባን ከዚያ ወስዶ በመሠዊያው ላይ ያቃጥለው፤ ከዚያም በኋላ ሴቲቱ ውሃውን እንድትጠጣ ያድርግ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ካህኑም ከእህሉ ቁርባን አንድ እፍኝ ሙሉ ለመታሰቢያው ወስዶ በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል፥ ከዚያም በኋላ ሴቲቱ ውኃውን እንድትጠጣ ያደርጋታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ ከእህሉ ቊርባን አንድ እፍኝ ወስዶ የመታሰቢያ ቊርባን ይሆን ዘንድ በመሠዊያው ላይ ያቃጥለው፤ በመጨረሻም ሴትዮዋ ውሃውን እንድትጠጣው ያድርግ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ካህኑም ከእህሉ ቍርባን አንድ እፍኝ ሙሉ ለመታሰቢያው ወስዶ በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል፥ ከዚያም በኋላ ለሴቲቱ ውኃውን ያጠጣታል። |
ወደ ካህኑ ወደ አሮን ልጆች ያመጣዋል፤ ከመልካም ስንዴ ዱቄቱና ከዘይቱም አንድ እፍኝ ሙሉና ነጩንም ዕጣን ሁሉ ወስዶ ካህኑ የእሳት ቍርባን ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ እንዲሆን ለመታሰቢያ በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል።
ካህኑም ከቍርባኑ መታሰቢያውን ይወስዳል፤ በመሠዊያውም ላይ ይጨምረዋል። ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ ያለው የሚቃጠል ቍርባን ነው።
ወደ ካህኑም ያመጣዋል፤ ካህኑም ስለ መታሰቢያው ለእርሱ እፍኝ ሙሉ ይዘግናል፤ ለእግዚአብሔርም በእሳት በተቃጠለው ቍርባን ላይ በመሠዊያው ላይ ይጨምረዋል፤ እርሱም የኀጢአት መሥዋዕት ነው።
ካህኑም ከእህሉ ቍርባን መልካሙን የስንዴ ዱቄት ከዘይት ጋር እፍኝ ሙሉ፥ ደግሞም በእህሉ ቍርባን ላይ ያለውን ዕጣን ሁሉ ያነሣል፤ ለእግዚአብሔርም በጎ መዓዛ ያለው የመታሰቢያ ቍርባን እንዲሆን ለመታሰቢያ ነውና በመሠዊያው ላይ ይጨምረዋል።
ካህኑም የቅንዐቱን መሥዋዕት ከሴቲቱ እጅ ይወስዳል፤ ያንም መሥዋዕት በእግዚአብሔር ፊት ያቀርበዋል፥ ወደ መሠዊያውም ያመጣዋል፤