Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘኍል 5:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ካህ​ኑም የቅ​ን​ዐ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት ከሴ​ቲቱ እጅ ይወ​ስ​ዳል፤ ያንም መሥ​ዋ​ዕት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያቀ​ር​በ​ዋል፥ ወደ መሠ​ዊ​ያ​ውም ያመ​ጣ​ዋል፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ካህኑ ለቅናት የቀረበውን የእህል ቍርባን ይቀበላት፤ በእግዚአብሔር ፊት ወዝውዞ ወደ መሠዊያው ያቅርበው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ካህኑም የቅንዓቱን የእህል ቁርባን ከሴቲቱ እጅ ይወስዳል፥ የእህሉንም ቁርባን በጌታ ፊት ይወዘውዘዋል፥ ወደ መሠዊያውም ያመጣዋል፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ካህኑ የዱቄቱን መባ ከሴትዮዋ እጅ ወስዶ ለእግዚአብሔር በመወዝወዝ የሚቀርብ የተለየ መሥዋዕት ይሆን ዘንድ በመሠዊያው ላይ ያቅርበው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ካህኑም የቅንዓቱን የእህል ቍርባን ከሴቲቱ እጅ ይወስዳል፥ የእህሉንም ቍርባን በእግዚአብሔር ፊት ይወዘውዘዋል፥ ወደ መሠዊያውም ያመጣዋል፤

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 5:25
6 Referencias Cruzadas  

ሁሉ​ንም በአ​ሮን እጆ​ችና በል​ጆቹ እጆች ታኖ​ረ​ዋ​ለህ፤ ለሚ​ለይ ቍር​ባን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ትለ​የ​ዋ​ለህ።


ሁሉ​ንም በአ​ሮ​ንና በል​ጆቹ እጆች ላይ አደ​ረገ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ቍር​ባ​ንን አቀ​ረበ፤


ያ ሰው ሚስ​ቱን ወደ ካህኑ ያም​ጣት፤ የኢፍ መስ​ፈ​ሪ​ያም ዐሥ​ረኛ እጅ ገብስ ዱቄት ቍር​ባን ስለ እር​ስዋ ያምጣ፤ የቅ​ን​ዐት ቍር​ባን ነውና፥ ኀጢ​አ​ት​ንም የሚ​ያ​ሳ​ስብ የመ​ታ​ሰ​ቢያ ቍር​ባን ነውና ዘይት አያ​ፍ​ስ​ስ​በት፤ ዕጣ​ንም አይ​ጨ​ም​ር​በት።


ካህ​ኑም ሴቲ​ቱን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያቆ​ማ​ታል፤ የሴ​ቲ​ቱ​ንም ራስ ይገ​ል​ጣል፤ በእ​ጅ​ዋም ለመ​ታ​ሰ​ቢያ የሚ​ሆ​ነ​ውን የእ​ህል ቍር​ባን፥ የቅ​ን​ዐት ቍር​ባን ያኖ​ራል፤ በካ​ህ​ኑም እጅ ርግ​ማ​ንን የሚ​ያ​መ​ጣው መራራ ውኃ ይሆ​ናል።


የመ​ር​ገ​ሙን መራራ ውኃ ለሴ​ቲቱ ያጠ​ጣ​ታል፤ የር​ግ​ማ​ኑም ውኃ ወደ ሆድዋ ይገ​ባል።


ካህ​ኑም ከእ​ህሉ ቍር​ባን አንድ እፍኝ ሙሉ ለመ​ታ​ሰ​ቢ​ያው ወስዶ በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ይጨ​ም​ረ​ዋል። ከዚ​ያም በኋላ ለሴ​ቲቱ ያን ውኃ ያጠ​ጣ​ታል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos