ዘኍል 33:47 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከጌልሞንዲብላታይምም ተጕዘው በናባው ፊት ባሉት በአባሪም ተራሮች ላይ ሰፈሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዓልሞን ዲብላታይም ተነሥተው በናባው አጠገብ በሚገኙት በዓባሪም ተራሮች ላይ ሰፈሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዓልሞንዲብላታይምም ተጉዘው በናባው ፊት ባሉ በዓብሪም ተራሮች ላይ ሰፈሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዓልሞንዲ ብላታይም ተነሥተው በመጓዝ በናባው ፊት ባሉት በዓብሪም ተራራዎች ላይ ሰፈሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዓልሞንዲብላታይምም ተጕዘው በናባው ፊት ባሉ በዓብሪም ተራሮች ላይ ሰፈሩ። |
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “ወደዚህ በናባው አሻገር ወዳለው ተራራ ውጣ፤ ለእስራኤልም ልጆች ይገዙአት ዘንድ እኔ የምሰጣቸውን የከነዓንን ምድር እያት፤
“በኢያሪኮ አንጻር በሞዓብ ምድር በዓባሪም ተራራ ውስጥ ወዳለው ወደ ናባው ተራራ ውጣ፤ ለእስራኤልም ልጆች ርስት አድርጌ የምሰጣቸውን የከነዓንን ምድር እያት፤
ሙሴም ከሞዓብ ሜዳ በኢያሪኮ ፊት ለፊት ወዳለው ወደ ናባው ተራራ ወደ ፈስጋ ራስ ወጣ፤ እግዚአብሔርም እስከ ዳን ድረስ ያለውን የገለዓድን ምድር አሳየው፤