ዘኍል 33:36 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከጋስዮንጋቤርም ተጕዘው በጺን ምድረ በዳ ሰፈሩ። ከጺን ምድረ በዳም ተጕዘው በፋራን ምድረ በዳ ሰፈሩ። ይህችም ቃዴስ ናት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዔጽዮንጋብር ተነሥተው በጺን ምድረ በዳ ባለችው በቃዴስ ሰፈሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዔጽዮንጋብርም ተጉዘው በጺን ምድረ በዳ ሰፈሩ፤ ይህችም ቃዴስ ናት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዔጽዮንጋብር ተነሥተው በመጓዝ በጺን ምድረ በዳ ሰፈሩ፤ ይህችም ቃዴስ ነች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዔጽዮንጋብርም ተጕዘው በጺን ምድረ በዳ ሰፈሩ፤ ይህችም ቃዴስ ናት። |
ገሥግሠውም በቃዴስ ፋራን ምድረ በዳ ወዳሉት ወደ ሙሴና ወደ አሮን፥ ወደ እስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ ደረሱ፤ ወሬውንም ለእነርሱና ለማኅበሩ ሁሉ ነገሩአቸው፤ የምድሪቱንም ፍሬ አሳዩአቸው።
የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ በመጀመሪያው ወር ወደ ጺን ምድረ በዳ መጡ፤ ሕዝቡም በቃዴስ ተቀመጡ፤ ማርያምም በዚያ ሞተች፤ ተቀበረችም።
እናንተ በጺን ምድረ በዳ በማኅበሩ ጠብ በቃሌ ላይ ዐምፃችኋልና፥ በእነርሱም ፊት በውኃው ዘንድ አላከበራችሁኝምና። ይህም በጺን ምድረ በዳ በቃዴስ ያለው የክርክር ውኃ ነው።”
በእስራኤል ልጆች መካከል በጺን ምድረ በዳ በቃዴስ ባለው በክርክር ውኃ ለቃሌ አልታዘዛችሁምና፥ በእስራኤልም ልጆች መካከል አልቀደሳችሁኝምና፥