ዔሳውም አባቱ ስለ ባረከው በያዕቆብ ቂም ያዘበት፤ ዔሳውም በልቡ አለ፥ “ለአባቴ የልቅሶ ቀን ትቅረብ፤ ወንድሜን ያዕቆብን እገድለዋለሁ።”
ዘኍል 20:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም፥ “በእኔ በኩል አታልፍም” አለ። የኤዶምያስም ንጉሥ በብዙ ሠራዊት በጽኑ እጅ ሊገጥመው ወጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኤዶምም እንደ ገና፣ “በዚህ ማለፍ አትችሉም” የሚል መልስ ሰጣቸው። ከዚያም ኤዶም ብዙና ኀይለኛ የሆነ ሰራዊት አሰልፎ ሊወጋቸው ወጣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም፦ “አታልፍም” አለ። ኤዶምያስም በብዙ ሕዝብና በጽኑ እጅ ሊገጥመው ወጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኤዶማውያን ግን “አይሆንም! አናሳልፋችሁም!” አሉ፤ ብርቱ የጦር ሠራዊትም አሰልፈው የእስራኤልን ሕዝብ ሊወጉ ወጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም፦ አታልፍም አለ። |
ዔሳውም አባቱ ስለ ባረከው በያዕቆብ ቂም ያዘበት፤ ዔሳውም በልቡ አለ፥ “ለአባቴ የልቅሶ ቀን ትቅረብ፤ ወንድሜን ያዕቆብን እገድለዋለሁ።”
የላካቸው መልእክተኞችም ወደ ያዕቆብ ተመልሰው እንዲህ አሉት፥ “ወደ ወንድምህ ወደ ዔሳው ሄደን ነበር፤ እርሱም ደግሞ ሊቀበልህ ይመጣል፤ ከእርሱም ጋር አራት መቶ ሰዎች አሉ።”
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦“ወንድሙን በሰይፍ አሳድዶታልና፥ በምድር ላይም ማኅፀንን አርክሶአልና፥ የሚዘልፈውንና የሚያስደነግጠውን በርብሮአልና፥ መዓቱንም ለዘለዓለም ጠብቆአልና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የኤዶምያስ ኀጢአት መቅሠፍቴን ከማድረግ አልመለስላቸውም።
የኤዶምያስም ንጉሥ “በእኔ በኩል አታልፍም፤ ይህ ካልሆነ ግን እንዋጋለን፤ በጦርም እቀበልህ ዘንድ እወጣለሁ” አለው።
እስራኤል ወደ ኤዶምያስ ንጉሥ፦ ‘በምድርህ እንዳልፍ፥ እባክህ፥ ፍቀድልኝ’ ብሎ መልእክተኞችን ላከ፤ የኤዶምያስም ንጉሥ እንቢ አለ። እንዲሁም ወደ ሞዓብ ንጉሥ ላከ፤ እርሱም እንቢ አለ።
ሴዎንም እስራኤል በድንበሩ እንዲያልፍ እንቢ አለ፤ ነገር ግን ሴዎን ሕዝቡን ሁሉ ሰበሰበ፤ በኢያሴርም ሰፈረ፤ ከእስራኤልም ጋር ተዋጋ።