በተማረኩበትም ሀገር ሆነው በልባቸው ንስሓ ቢገቡ፥ በተማረኩበትም ሀገር ሳሉ ተመልሰው፦ ኀጢአት ሠርተናል፥ በድለንማል፥ ክፉንም አድርገናል ብለው ቢለምኑህ፥
ነህምያ 9:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም ልጆች ከባዕድ ሕዝብ ሁሉ ራሳቸውን ለዩ፤ ቆመውም ኀጢአታቸውንና የአባቶቻቸውን ኀጢአት ተናዘዙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእስራኤላውያን ዘር የሆኑትም ራሳቸውን ከባዕዳን ሁሉ ለዩ። ቆመውም ኀጢአታቸውንና የአባቶቻቸውን በደል ተናዘዙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤል ዘር ከባዕድ ሕዝቦች ሁሉ ራሳቸውን ለዩ፥ ቆመውም ኃጢአታቸውንና የአባቶቻቸውን በደል ተናዘዙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ራሳቸውንም ከባዕዳን ሕዝቦች ሁሉ ለዩ፤ ከዚህም በኋላ ሁሉም ተነሥተው በመቆም፥ እነርሱና የቀድሞ አባቶቻቸው የሠሩትን ኃጢአት ሁሉ ተናዘዙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም ዘር ከእንግዶች ሁሉ ራሳቸውን ለዩ፥ ቆመውም ኃጢአታቸውንና የአባቶቻቸውን ኃጢአት ተናዘዙ። |
በተማረኩበትም ሀገር ሆነው በልባቸው ንስሓ ቢገቡ፥ በተማረኩበትም ሀገር ሳሉ ተመልሰው፦ ኀጢአት ሠርተናል፥ በድለንማል፥ ክፉንም አድርገናል ብለው ቢለምኑህ፥
አሁንም የአባቶቻችንን አምላክ እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ደስ የሚያሰኘውንም አድርጉ፤ ከምድርም አሕዛብና ከእንግዶች ሴቶች ተለዩ” አላቸው።
ከምርኮም ተመልሰው የመጡት የእስራኤል ልጆች፥ የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን ይፈልጉ ዘንድ ራሳቸውን ከምድር አሕዛብ ርኵሰት ለይተው ወደ እነርሱ መጥተው የነበሩት ሁሉ ፋሲካውን በሉ፤
ይህም ከተፈጸመ በኋላ የሕዝቡ አለቆች ወደ እኔ ቀርበው፥ “የእስራኤል ሕዝብ ካህናቱም፥ ሌዋውያኑም፥ እንደ ከነዓናውያን፥ እንደ ኬጤዎናውያን፥ እንደ ፌርዜዎናውያን፦ እንደ ኢያቡሴዎናውያን፥ እንደ አሞናውያን፥ እንደ ሞዓባውያን፥ እንደ ግብፃውያንና እንደ አሞራውያን ርኵሰት ያደርጋሉ እንጂ ከምድር አሕዛብ አልተለዩም፤
አቤቱ የእስራኤል አምላክ ሆይ፥ አንተ ጻድቅ ነህ፤ ዛሬም እንደ ሆነው እኛ አምልጠን ቀርተናል፤ እነሆ በፊትህ በበደላችን አለን፤ ስለዚህ በፊትህ ሊቆም የሚችል የለም።”
ለራሳቸውና ለልጆቻቸውም ሴቶች ልጆቻቸውን ወስደዋል፤ የተቀደሰውንም ዘር ከምድር አሕዛብ ጋር ደባልቀዋል፤ አስቀድሞም አለቆቹና ሹሞቹ በዚህ መተላለፍ መጀመሪያ ሆነዋል” አሉኝ።
እኔ ባሪያህ ዛሬ በፊትህ ስለ ባሪያዎችህ ስለ እስራኤል ልጆች ሌሊትና ቀን የምጸልየውን ጸሎት ትሰማ ዘንድ ጆሮዎችህ ያድምጡ፤ ዐይኖችህም ይከፈቱ፤ በአንተ ላይም ያደረግነውን የእስራኤልን ልጆች ኀጢአት ለአንተ እንናዘዛለን፤ እኔም፥ የአባቴም ቤት በድለናል።
የቀሩትም ሕዝብ፥ ካህናቱም፥ ሌዋውያኑም፥ በረኞቹም፥ መዘምራንም፥ ናታኒምም፥ ከምድርም አሕዛብ ራሳቸውን የለዩና ወደ እግዚአብሔር ሕግ የገቡ ሁሉ፥ ሚስቶቻቸውም፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውም፥ የሚያውቁትና የሚያስተውሉትም ሁሉ ወንድሞቻቸውንና ታላላቆቻቸውን አበረታቱ፤
በእግዚአብሔርም ባሪያ በሙሴ እጅ በተሰጠው በእግዚአብሔር ሕግ ይሄዱ ዘንድ፥ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ሁሉ፥ ፍርዱንም፥ ሥርዐቱንም ይጠብቁና ያደርጉ ዘንድ ርግማንንና መሐላን አደረጉ።
ሕዝቡን የያዕቆብን ቤት ትቶአልና፤ ምድራቸው እንደ ቀድሞው እንደ ፍልስጥኤማውያን ምድር በሟርት ተሞልቶአልና፤ እንደ ባዕድ ልጆችም ሆነዋልና፤ ብዙ እንግዶች ልጆችም ተወልደውላቸዋልና።
በአምላክሽ በእግዚአብሔር ላይ እንዳመፅሽ፥ መንገድሽንም ከለመለመ ዛፍ ሁሉ በታች ለእንግዶች እንደ ዘረጋሽ፥ ቃሌንም እንዳልሰማሽ ኀጢአትሽን ብቻ ዕወቂ ይላል እግዚአብሔር።
ዲቃሎችን ልጆች ወልደዋልና እግዚአብሔርን ከድተዋል፤ አሁንም ኵብኵባ እነርሱንና ርስታቸውን ይበላቸዋል።