ሚክያስ 1:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቁስልዋ የማይፈወስ ነውና፥ እስከ ይሁዳም ደርሶአልና፥ ወደ ሕዝቤም በር ወደ ኢየሩሳሌም ቀርቦአልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቍስሏ የማይሽር ነውና፤ ለይሁዳ ተርፏል፤ እስከ ሕዝቤ መግቢያ በር፣ እስከ ኢየሩሳሌም እንኳ ደርሷል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቁስልዋ የማይፈወስ ነውና፤ ወደ ይሁዳ መጥቷል፥ ወደ ሕዝቤ በር ወደ ኢየሩሳሌምም ደርሶአል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሰማርያ ቊስል ሊፈወስ የሚችል አይደለም፤ ይህም ሥቃይ ወደ ይሁዳ ደርሶአል፤ ሕዝቤ ወደሚሰበሰቡበት ወደ ኢየሩሳሌም አደባባይም ተዛምቶአል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቁስልዋ የማይፈወስ ነውና፥ እስከ ይሁዳም ደርሶአልና፥ ወደ ሕዝቤም በር ወደ ኢየሩሳሌም ቀርቦአልና። |
እንዲህም ሆነ፤ በንጉሡ በሕዝቅያስ በዐሥራ አራተኛው ዓመተ መንግሥት የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም ወደ ይሁዳ ወደ ተመሸጉት ከተሞች ሁሉ ወጥቶ ወሰዳቸው።
የአሦርም ንጉሥ ራፋስቂስን ከብዙ ሠራዊት ጋር ከለኪሶ ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝቅያስ ወደ ኢየሩሳሌም ላከው፤ እርሱም በአጣቢው እርሻ መንገድ ባለችው በላይኛዪቱ ኵሬ መስኖ አጠገብ ቆመ።
የሚያሳዝኑኝ በእኔ ላይ ለምን ይበረታሉ? ቍስሌስ ስለ ምን የማይፈወስ ሆነ? ስለ ምንስ አልሽርም አለ? እንደ ሐሰተኛ ምንጭ፥ እንዳልታመነች ውኃም ሆነብኝ።
ድንግሊቱ የግብፅ ልጅ ሆይ! ወደ ገለዓድ ውጪ፤ የሚቀባ መድኀኒትንም ውሰጂ፤ ለምንም የማይጠቅምሽን መድኀኒት በከንቱ አብዝተሻል።
ስብራትህ አይፈወስም፥ ቁስልህም ክፉ ነው፣ ወሬህንም የሚሰሙ ሁሉ እጃቸውን በአንተ ላይ ያጨበጭባሉ፣ ክፋትህ ሁልጊዜ ያላለፈችበት ሰው ማን ነውና?