ሚልክያስ 2:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቃል ኪዳኔ ከሌዊ ጋር ይሆን ዘንድ ይህን ትእዛዝ እንደ ሰደድሁላችሁ ታውቃላችሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሌዊ ጋራ የገባሁት ኪዳን ይጸና ዘንድ፣ ይህን ማስጠንቀቂያ የላክሁት እኔ መሆኔንም ታውቃላችሁ” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቃል ኪዳኔ ከሌዊ ጋር ለማድረግ ይህን ትእዛዝ እንደ ላክሁላችሁ ታውቃላችሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሌዊና ከተወላጆቹ ጋር ያለኝ ቃል ኪዳን ጸንቶ ይኖር ዘንድ ይህን ትእዛዝ እኔ የላክሁላችሁ መሆኑን ታውቃላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቃል ኪዳኔ ከሌዊ ጋር ይሆን ዘንድ ይህን ትእዛዝ እንደ ሰደድሁላችሁ ታውቃላችሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። |
አቤቱ፥ ከፍ ያለች ክንድህን አላወቁም፤ ካወቁ ግን ያፍራሉ። አላዋቆች ሰዎችን ቅንአት ያዛቸው፤ አሁንም እሳት ጠላቶችን ትበላለች።
ስለዚህም የማምለኪያ ዐፀዶችና የፀሐይ ምስሎች ዳግመኛ እንዳይነሡ የመሠዊያውን ድንጋይ ሁሉ እንደ ደቀቀ እንደ ኖራ ድንጋይ ባደረገ ጊዜ ፥ እንዲሁ የያዕቆብ በደል ይሰረያል፤ ይህም ኀጢአትን የማስወገድ ፍሬ ሁሉ ነው።
ስለ ሰላም ትንቢት የተናገረ ነቢይ ትንቢቱ በደረሰ ጊዜ፥ እግዚአብሔር በእውነት የላከው ነቢይ እንደ ሆነ ይታወቃል።”
ታላቅ እሆናለሁ፤ እቀደስማለሁ፤ እመሰገናለሁም፤ በብዙ አሕዛብም ዐይን የታወቅሁ እሆናለሁ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
እንጀራዬን፥ ስብንና ደምን በምታቀርቡበት ጊዜ በመቅደሴ ውስጥ ይሆኑ ዘንድ ቤቴንም ያረክሱ ዘንድ፥ በልባቸውና በሥጋቸው ያልተገረዙትን እንግዶችን ሰዎች አግብታችኋልና፥ በርኵሰታችሁም ሁሉ ቃል ኪዳኔን አፍርሳችኋልና።
እነሆ፥ መልእክተኛዬን እልካለሁ፥ መንገድንም በፊቴ ያስተካክላል፣ እናንተም የምትፈልጉት ጌታ በድንገት ወደ መቅደሱ ይመጣል፣ የምትወዱትም የቃል ኪዳን መልእክተኛ፥ እነሆ፥ ይመጣል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
ደግሞም የአባትህን የሌዊን ነገድ ወንድሞችህን ወደ አንተ ሰብስብ፤ ከአንተም ጋር በአንድነት ይሁኑ፤ ያገልግሉህም፤ አንተ ከአንተም ጋር ልጆችህ በምስክሩ ድንኳን ፊት ትሆናላችሁ።
“ለሌዊም ልጆች እነሆ፥ በምስክሩ ድንኳን አገልግሎት ስለሚያገለግሉ፥ የእስራኤልን ልጆች ዐሥራት ርስት አድርጌ ሰጥቻቸዋለሁ።
“እነሆ፥ እኔ በእስራኤል ልጆች ዘንድ መጀመሪያ በሚወለደው በበኵር ሁሉ ፋንታ ሌዋውያንን ከእስራኤል ልጆች መካከል ለይች ወስጃለሁ፤ በእነርሱ ፋንታ ሌዋውያን ለእኔ ይሁኑ፤
“ሌዋውያንን በእስራኤል ልጆች በኵር ሁሉ ፋንታ፥ የሌዋውያንንም እንስሶች በእንስሶቻቸው ፋንታ ውሰድ፤ ሌዋውያንም ለእኔ ይሁኑ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝና።
ከከተማችሁ የተጣበቀብንን ትቢያ እንኳን እናራግፍላችኋለን፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ እንደ ቀረበች ይህን ዕወቁ።
በእኔ ያለውን፥ ፍሬ የማያፈራውን ቅርንጫፍም ሁሉ ያስወግደዋል፤ የሚያፈራውን ቅርንጫፍ ሁሉ ግን በብዙ እንዲያፈራ ያጠራዋል።