La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘሌዋውያን 8:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ልብሰ እን​ግ​ድ​ዓ​ው​ንም በእ​ርሱ ላይ አደ​ረገ፤ በል​ብሰ እን​ግ​ድ​ዓ​ውም ላይ የም​ል​ክ​ትና የእ​ው​ነት መገ​ለ​ጫ​ዎ​ችን አኖ​ረ​በት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የደረት ኪሱን በላዩ አደረገለት፤ በደረት ኪሱም ውስጥ ኡሪምንና ቱሚምን አኖረ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የደረት ኪስ በእርሱ ላይ አደረገ፤ በደረቱ ኪስም ውስጥ ኡሪምንና ቱሚምን አኖረበት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በኤፉዱም ላይ የደረት ኪስ ሰፍቶ የእግዚአብሔር ፈቃድ የሚገለጥባቸውን ኡሪምና ቱሚምን አኖረ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የደረት ኪስ በእርሱ ላይ አደረገ፤ በደረቱ ኪስም ውስጥ ኡሪምንና ቱሚምን አኖረበት።

Ver Capítulo



ዘሌዋውያን 8:8
13 Referencias Cruzadas  

ሐቲ​ር​ሰ​ስ​ታም፥ “በኡ​ሪ​ምና በቱ​ሚም የሚ​ፈ​ርድ ካህን እስ​ኪ​ነሣ ድረስ ከቅ​ዱሰ ቅዱ​ሳኑ አት​በ​ሉም” አላ​ቸው።


ሐቴ​ር​ሰ​ታም፥ “በኡ​ሪ​ምና በቱ​ሚም የሚ​ፈ​ርድ ካህን እስ​ኪ​ነሣ ድረስ ከተ​ቀ​ደ​ሰው ነገር አት​በ​ሉም” አላ​ቸው።


“እኔ​ንም በክ​ህ​ነት እን​ዲ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉኝ ትቀ​ድ​ሳ​ቸው ዘንድ የም​ታ​ደ​ር​ግ​ላ​ቸው ነገር ይህ ነው፤ ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውን አንድ ወይ​ፈ​ንና ሁለት አውራ በጎች ትወ​ስ​ዳ​ለህ።


እንደ ቀለ​በት በል​ብህ፥ እንደ ቀለ​በ​ትም ማኅ​ተም በክ​ን​ድህ አኑ​ረኝ፤ ፍቅር እንደ ሞት የበ​ረ​ታች ናትና፥ ቅን​ዐ​ትም እንደ ሲኦል የጨ​ከ​ነች ናትና። ላን​ቃዋ እንደ እሳት ላንቃ እንደ ነበ​ል​ባል ነው።


ጽድ​ቅ​ንም እንደ ጥሩር ለበሰ፤ በራ​ሱም ላይ የማ​ዳ​ንን ራስ ቍር አደ​ረገ፤ የበ​ቀ​ል​ንም ልብስ ለበሰ።


በካ​ህ​ኑም በአ​ል​ዓ​ዛር ፊት ይቁም፤ እር​ሱም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ፍርድ ይጠ​ይ​ቅ​ለት፤ እርሱ ከእ​ር​ሱም ጋር የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማኅ​በር ሁሉ በቃሉ ይውጡ፤ በቃ​ሉም ይግቡ።”


እን​ግ​ዲህ ወገ​ባ​ች​ሁን በእ​ው​ነት ታጥ​ቃ​ችሁ ቁሙ፤ የጽ​ድ​ቅ​ንም ጥሩር ልበሱ።


ስለ ሌዊም እን​ዲህ አለ፥ ለሌዊ ቃሉን፥ በመ​ከ​ራም ለፈ​ተ​ኑት፥ በክ​ር​ክር ውኃም ለሰ​ደ​ቡት፥ ለእ​ው​ነ​ተ​ኛው ሰው ጽድ​ቁን መልስ።


እኛ ግን ከቀን ስለ ሆንን፥ የእምነትንና የፍቅርን ጥሩር የመዳንንም ተስፋ እንደ ራስ ቁር እየለበስን በመጠን እንኑር፤


ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ነገድ ሁሉ ካህን ይሆ​ነኝ ዘንድ፥ በመ​ሠ​ዊ​ያ​ዬም ላይ ይሠዋ ዘንድ፥ ዕጣ​ን​ንም ያጥን ዘንድ፥ ኤፉ​ድ​ንም በፊቴ ይለ​ብስ ዘንድ፥ የአ​ባ​ት​ህን ቤት ለእኔ መረ​ጥ​ሁት፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች የእ​ሳት ቍር​ባን ሁሉ ስለ ምግብ ለአ​ባ​ትህ ቤት ሰጠሁ።


ሳኦ​ልም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ጠየቀ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሕ​ልም አላ​ሚ​ዎች፥ ወይም በነ​ጋ​ሪ​ዎች፥ ወይም በነ​ቢ​ያት አል​መ​ለ​ሰ​ለ​ትም።