ዘሌዋውያን 21:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ነውረኛ ነውና መቅደሶችን እንዳያረክስ ወደ መጋረጃው አይግባ፤ ወደ መሠዊያውም አይቅረብ፤ የምቀድሳቸው እኔ እግዚአብሔር ነኝና።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን እንከን ያለበት ስለ ሆነ መቅደሴን እንዳያረክስ ወደ መጋረጃው አይቅረብ ወይም ወደ መሠዊያው አይጠጋ፤ የምቀድሳቸው እኔ እግዚአብሔር ነኝ።’ ” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ነውረኛ ነውና መቅደሶቼን እንዳያረክስ ወደ መጋረጃው አይግባ፥ ወደ መሠዊያውም አይቅረብ፤ የምቀድሳቸው እኔ ጌታ ነኝና።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን የአካል ጒድለት ስላለበት ወደተቀደሰው መጋረጃ ወይም ወደ መሠዊያው አይቅረብ፤ እነዚህን ለእኔ የተቀደሱትን ነገሮች ማርከስ የለበትም፤ እነርሱንም የቀደስኳቸው እኔ እግዚአብሔር ነኝ።’ ” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ነውረኛ ነውና መቅደሶቼን እንዳያረክስ ወደ መጋረጃው አይግባ፥ ወደ መሠዊያውም አይቅረብ፤ የምቀድሳቸው እኔ እግዚአብሔር ነኝ። |
“እንዲሁም በእነርሱ መካከል ያለችውን ድንኳኔን ባረከሱ ጊዜ፥ በርኩስነታቸው እንዳይሞቱ የእስራኤልን ልጆች ከርኩስነታቸው አንጹአቸው።
የአምላኩም ቅባት ዘይት ቅዱስነት በላዩ ነውና ከመቅደስ አይውጣ፤ የአምላኩንም ቅዱስ ስም አያርክስ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።
ለአምላካቸው ቅዱሳን ይሁኑ፤ የአምላካቸውንም ስም አያርክሱ፤ የእግዚአብሔርን መሥዋዕትና የአምላካቸውን መባ ያቀርባሉና ቅዱሳን ይሁኑ።
በኀጢአት ሳሉ ከተቀደሰው መሥዋዕት ከበሉ ግን ኀጢአትና በደል ይሆንባቸዋል፤ የማነጻቸው እኔ እግዚአብሔር ነኝና።”