ዘሌዋውያን 21:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 ለአምላካቸው ቅዱሳን ይሁኑ፤ የአምላካቸውንም ስም አያርክሱ፤ የእግዚአብሔርን መሥዋዕትና የአምላካቸውን መባ ያቀርባሉና ቅዱሳን ይሁኑ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም6 ለአምላካቸው የተቀደሱ ይሁኑ፤ የአምላካቸውንም ስም አያርክሱ። ለእግዚአብሔር በእሳት የሚቀርበውን መሥዋዕት የአምላካቸውን ምግብ ስለሚያቀርቡ ቅዱሳን ይሁኑ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 ለአምላካቸው የተቀደሱ ይሆናሉ፥ የአምላካቸውንም ስም አያረክሱም፤ እነርሱም የአምላካቸው እንጀራ የሆነውን፥ ለጌታ በእሳት የሚቀርበውን ቁርባን ያቀርባሉና የተቀደሱ ይሆናሉ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 የሚቃጠል መሥዋዕትና የምግብ መባ ለእኔ ለአምላካቸው የሚያቀርቡ ካህናት ለእኔ የተለዩና ስሜንም የማያረክሱ መሆን አለባቸው፤ ስለዚህ የተቀደሱ ይሆናሉ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 ለአምላካቸው ቅዱሳን ይሁኑ፥ የአምላካቸውንም ስም አያጐስቍሉ፤ የእግዚአብሔርን የእሳት ቍርባንና የአምላካቸውን እንጀራ ያቀርባሉና ቅዱሳን ይሁኑ። Ver Capítulo |