እነርሱም አሉ፥ “ባሪያዎችህ በከነዓን ምድር የምንኖር ዐሥራ ሁለት ወንድማማቾች ነን፤ ታናሹም እነሆ ዛሬ ከአባታችን ጋር ነው፤ ሌላውም ሞቶአል።”
ሰቈቃወ 5:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አባቶቻችን ኀጢአትን ሠሩ፤ ዛሬም የሉም፤ እኛም በደላቸውን ተሸከምን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አባቶቻችን ኀጢአት ሠርተው ዐለፉ፤ እኛም የእነርሱን ቅጣት ተሸከምን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አባቶቻችን ኃጢአትን ሠሩ ዛሬም የሉም፥ እኛም በደላቸውን ተሸከምን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አባቶቻችን ኃጢአት ሠርተው አለፉ፤ እኛ ግን የእነርሱን ኃጢአት እንሸከማለን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አባቶቻችን ኃጢአትን ሠሩ ዛሬም የሉም፥ እኛም በደላቸውን ተሸከምን። |
እነርሱም አሉ፥ “ባሪያዎችህ በከነዓን ምድር የምንኖር ዐሥራ ሁለት ወንድማማቾች ነን፤ ታናሹም እነሆ ዛሬ ከአባታችን ጋር ነው፤ ሌላውም ሞቶአል።”
አባታቸው ያዕቆብም እንዲህ አላቸው፥ “ልጅ አልባ አስቀራችሁኝ፤ ዮሴፍ የለም፤ ስምዖንም የለም፤ ብንያምንም ትወስዱብኛላችሁ፤ ይህ ሁሉ በእኔ ላይ ደረሰ።”
ስለ ምን መተላለፌን ይቅር አትልም? ኀጢአቴንስ ስለ ምን አታነጻም? አሁን በምድር ውስጥ እተኛለሁ፤ በማለዳም አልነቃም።”
አትስገድላቸው፤ አታምልካቸውም፤ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና። በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኀጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፤
አንተ እንዲህ ትላቸዋለህ፦ አባቶቻችሁ እኔን ስለ ተዉ ነው፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ሌሎችንም አማልክት ተከተሉ፤ አመለኩአቸውም፤ ሰገዱላቸውም፤ እነርሱም ትተውኛል፤ ሕጌንም አልጠበቁም፤
እናንተም ከአባቶቻችሁ ይልቅ ክፉ አድርጋችኋል፤ እነሆም ሁላችሁ እንደ ክፉ ልባችሁ ፍላጎት ሄዳችኋል፤ እኔንም አልሰማችሁም።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “የኀዘን፥ የልቅሶና የጩኸት ድምፅ በራማ ተሰማ፤ ራሔል ስለ ልጆችዋ አለቀሰች፤ የሉምና ስለ ልጆችዋ መጽናናትን እንቢ አለች።
“በእስራኤል ልጆች፦ ‘አባቶች ጨርቋ የወይን ፍሬ በሉ፥ የልጆችም ጥርሶች ጠረሱ’ ብላችሁ በመካከላችሁ የምትመስሉት ምሳሌ ምንድን ነው?
እግዚአብሔር መዓቱ የራቀ ምሕረቱ የበዛ ጻድቅ፥ አበሳን፥ መተላለፍንና ኀጢአትን ይቅር የሚል፥ ኀጢአተኞችንም ከቶ የማያነጻ፥ የአባቶችን ኀጢአት እስከ ሦስትና አራት ትውልድ ድረስ በልጆች ላይ የሚያመጣ ነው።