La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሰቈቃወ 5:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ግብ​ፃ​ው​ያ​ንና አሦ​ራ​ው​ያን፥ እን​ጀ​ራን ያጠ​ግ​ቡን ዘንድ እጃ​ቸ​ውን ሰጡን።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እንጀራ እንጠግብ ዘንድ፣ ለአሦርና ለግብጽ እጃችንን ሰጠን።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ለግብጻውያንና ለአሦራውያን እንጀራ እንጠግብ ዘንድ እጅ ሰጠን።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በቂ ምግብ ለማግኘት ለግብጽና ለአሦር እጃችንን ሰጠን፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ለግብጻውያንና ለአሦራውያን እንጀራ እንጠግብ ዘንድ እጅ ሰጠን።

Ver Capítulo



ሰቈቃወ 5:6
15 Referencias Cruzadas  

አብ​ር​ሃ​ምም ሎሌ​ውን፥ የቤ​ቱን ሽማ​ግሌ፥ የከ​ብ​ቱን ሁሉ አዛዥ አለው፦


ከዚ​ያም በሄደ ጊዜ የሬ​ካ​ብን ልጅ ኢዮ​ና​ዳ​ብን በመ​ን​ገድ አገ​ኘው፤ ተቀ​ብ​ሎም መረ​ቀው፤ ኢዩም፥ “ልቤ ከል​ብህ ጋር ቅን እንደ ሆነ ያህል ልብህ ከልቤ ጋር በቅ​ን​ነት ነውን?” አለው። ኢዮ​ና​ዳ​ብም፥ “አዎን” አለው። ኢዩም፥ “እው​ነ​ት​ህስ ከሆነ እጅ​ህን ስጠኝ” አለ። እጁ​ንም ሰጠው፤ ወደ እር​ሱም ወደ ሰረ​ገ​ላው አወ​ጣው።


ዝሙ​ት​ሽን ከእ​ነ​ርሱ ጋር አበ​ዛሽ፤ ከአ​ንቺ የራቁ ብዙ​ዎ​ች​ንም ተጐ​ዳ​ኘሽ። መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ች​ሽ​ንም ወደ ሩቅ ላክሽ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ተወ​ገ​ድሽ፤ እስከ ሲኦ​ልም ድረስ ተዋ​ረ​ድሽ።


አሁ​ንስ የግ​ዮ​ንን ውኃ ትጠጪ ዘንድ በግ​ብፅ መን​ገድ ምን ጉዳይ አለሽ? የወ​ን​ዞ​ች​ንም ውኃ ትጠጪ ዘንድ በአ​ሦር መን​ገድ ምን ጉዳይ አለሽ?


መን​ገ​ድ​ሽን እጥፍ ታደ​ርጊ ዘንድ ለምን እጅግ ትሮ​ጫ​ለሽ? በአ​ሦር እን​ዳ​ፈ​ርሽ በግ​ብ​ፅም ታፍ​ሪ​ያ​ለሽ።


እጆ​ችዋ ደክ​መ​ዋ​ልና ክበ​ቡ​አት፤ ግንቧ ወድ​ቋል፤ ቅጥ​ር​ዋም ፈር​ሶ​አል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በቀል ነውና ተበ​ቀ​ሏት፤ እንደ ሠራ​ች​ውም ሥሩ​ባት።


ፌ። በማ​ያ​ድን ወገን እያ​መ​ንን ረዳ​ታ​ችን ከንቱ ስለ ሆነ፥ እኛ ገና በሕ​ይ​ወት ሳለን ዐይ​ኖ​ቻ​ችን ጠፉ።


ቃል ኪዳ​ኑ​ንም በማ​ፍ​ረስ መሐ​ላ​ውን ንቆ​አል፤ እነ​ሆም እጁን አሳ​ልፌ ሰጠሁ፤ ይህ​ንም ሁሉ አድ​ር​ጎ​አል፤ ስለ​ዚ​ህም አያ​መ​ል​ጥም።


ኤፍ​ሬም በሐ​ሰት፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤትና ይሁ​ዳም በተ​ን​ኰል ከበ​ቡኝ፤ አሁ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዐወ​ቃ​ቸው፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቅዱስ ሕዝብ ተባሉ።


ኤፍ​ሬ​ምም ደዌ​ውን አያት፤ ይሁ​ዳም ሥቃ​ዩን አያት፤ ኤፍ​ሬም ወደ አሦር ሄደ፤ ወደ ንጉ​ሡም ወደ ኢያ​ሪም መል​እ​ክ​ተ​ኛን ላከ፤ እርሱ ግን ፈጽሞ ይፈ​ው​ሳ​ችሁ ዘንድ አል​ቻ​ለም፤ ከእ​ና​ን​ተም ሕማም አል​ተ​ወ​ገ​ደም።


ኤፍ​ሬ​ምም ልብ እን​ደ​ሌ​ላት እንደ ሰነፍ ርግብ ነው፤ ግብ​ፅን ጠሩ፤ ወደ አሦ​ርም ሄዱ።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምድር ላይ አይ​ቀ​መ​ጡም፤ ኤፍ​ሬ​ምም በግ​ብፅ ይቀ​መ​ጣል፤ በአ​ሦ​ርም ርኩስ ነገ​ርን ይበ​ላሉ።