ኢያሱ 24:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለይስሐቅም ያዕቆብንና ዔሳውን ሰጠሁት፤ ለዔሳውም የሴይርን ተራራ ርስት አድርጌ ሰጠሁት፤ የያዕቆብም ልጆች ወደ ግብፅ ወረዱ፤ በዚያም ታላቅ ሕዝብ ሆኑ፤ በዙም፤ በረቱም፤ ግብፃውያንም መከራ አጸኑባቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለይሥሐቅ ያዕቆብንና ዔሳውን ሰጠሁት፤ ለዔሳውም ኰረብታማውን የሴይርን ምድር ርስት አድርጌ ሰጠሁት፤ ያዕቆብና ልጆቹ ግን ወደ ግብጽ ወረዱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለይስሐቅም ያዕቆብንና ዔሳውን ሰጠሁት፤ ለዔሳውም የሴይርን ተራራ ርስት አድርጌ ሰጠሁት፤ ያዕቆብም ልጆቹም ወደ ግብጽ ወረዱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለይስሐቅም ያዕቆብንና ዔሳውን ሰጠሁ፤ ለዔሳውም የኤዶምን ኮረብታማ አገር ርስት አድርጌ ሰጠሁት፤ ነገር ግን ያዕቆብና ልጆቹ ወደ ግብጽ ወረዱ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለይስሐቅም ያዕቆብንና ዔሳውን ሰጠሁት፥ ለዔሳውም የሴይርን ተራራ ርስት አድርጌ ሰጠሁት፥ ያዕቆብም ልጆቹም ወደ ግብፅ ወረዱ። |
እንዳያጠፋቸው የቍጣውን መቅሠፍት ይመልስ ዘንድ የተመረጠው ሙሴ በመቅሠፍት ጊዜ በፊቱ ባይቆም ኖሮ፥ ባጠፋቸው ነበር አለ።
ሚስትህ በቤትህ እልፍኝ ውስጥ እንደሚያፈራ ወይን ትሆናለች፤ ልጆችህም በማዕድህ ዙሪያ እንደ አዲስ የወይራ ተክል ይሆናሉ።
የሴይርን ተራራ ለዔሳው ልጆች ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ እኔ ከምድራቸው የጫማ መርገጫ ታህል እንኳን አልሰጣችሁምና አትጣሉአቸው።