አትስገድላቸው፤ አታምልካቸውም፤ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና። በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኀጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፤
ዮሐንስ 15:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሌላ ያልሠራውን ሥራ በመካከላቸው ባልሠራ ኖሮ ኀጢአት ባልሆነባቸውም ነበር፤ አሁን ግን እኔንም አባቴንም አይተዋል፤ ጠልተውማል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሌላ ሰው ያላደረገውን በመካከላቸው ባላደርግ ኖሮ፣ ኀጢአት ባልሆነባቸው ነበር፤ አሁን ግን እነዚህን ታምራት አይተዋል፤ ሆኖም እኔንም አባቴንም ጠልተዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሌላ ሰው ያላደረገውን ሥራ በመካከላቸው ባላደርግ ኖሮ ኃጢአት ባልሆነባቸው ነበር፤ አሁን ግን እኔንም አባቴንም አይተዋል፤ ጠልተውማል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሌላ ሰው ያላደረገውን ሥራ በመካከላቸው ባላደርግ ኖሮ ኃጢአት ባልሆነባቸውም ነበር፤ አሁን ግን ይህን ሁሉ ካዩ በኋላ እኔንም አባቴንም ጠልተዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሌላ ሰው ያላደረገውን ሥራ በመካከላቸው ባላደረግሁ፥ ኃጢአት ባልሆነባቸውም ነበር፤ አሁን ግን እኔንም አባቴንም አይተውማል ጠልተውማል። |
አትስገድላቸው፤ አታምልካቸውም፤ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና። በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኀጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፤
ዮሐንስ በጽድቅ መንገድ መጥቶላችሁ ነበርና፤ አላመናችሁበትም፤ ቀራጮችና ጋለሞቶች ግን አመኑበት፤ እናንተም ይህን አይታችሁ ታምኑበት ዘንድ በኋላ ንስሐ አልገባችሁም።
ተነሥቶም ወዲያው አልጋውን ተሸክሞ በሁሉ ፊት ወጣ፤ ስለዚህም ሰዎች ሁሉ ተገረሙና “እንዲህ ያለ ከቶ አላየንም፤” ብለው እግዚአብሔርን አከበሩ።
ጌታችን ኢየሱስም፥ “ይህ ምንድነው?” አላቸው፤ እነርሱም እንዲህ አሉት፥ “በእግዚአብሔር ፊትና በሕዝቡ ሁሉ ፊት በቃሉና በሥራው ብርቱ ነቢይና እውነተኛ ሰው ስለነበረው ስለ ናዝሬቱ ስለ ኢየሱስ፥
ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፥ “ከአባቴ ብዙ መልካም ሥራ አሳየኋችሁ፤ ከእነርሱ በየትኛው ሥራ ምክንያት ትወግሩኛላችሁ?”
ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አለው፥ “ፊልጶስ፥ ይህን ያህል ዘመን አብሬአችሁ ስኖር አታወቀኝምን? እኔን ያየ አብን አየ፤ እንግዲህ እንዴት አብን አሳየን ትላለህ?
ባልመጣሁና ባልነገርኋቸውስ ኖሮ ኀጢአት ባልሆነባቸውም ነበር፤ አሁን ግን ለኀጢአታቸው ምክንያት የላቸውም።
እርሱም በሌሊት ወደ ጌታችን ኢየሱስ መጥቶ እንዲህ አለው፥ “መምህር ሆይ፥ ልታስተምር ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ መጣህ እናውቃለን፤ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ከሆነ በቀር አንተ የምታደርገውን ይህን ተአምር ሊያደርግ የሚችል የለምና።”
እኔ ግን ከዮሐንስ ምስክርነት የሚበልጥ ምስክር አለኝ፤ ልሠራውና ልፈጽመው አባቴ የሰጠኝ ሥራ፥ አብ እንደ ላከኝ ያ የምሠራው ሥራ ምስክሬ ነውና።
ከሕዝቡም ብዙዎች አመኑበትና፥ “በውኑ ክርስቶስ በሚመጣበት ጊዜ ይህ ሰው ካደረገው ተአምራት የሚበልጥ ያደርጋልን?” አሉ።
ጌታችን ኢየሱስም፥ “ዕዉሮችስ ብትሆኑ ኀጢኣት ባልሆነባችሁም ነበር፤ አሁን ግን እናያለን ትላላችሁ፤ አታዩምም፤ ስለዚህም ኀጢኣታችሁ ጸንቶ ይኖራል” አላቸው።
ስለ ናዝሬቱ ስለ ኢየሱስ እግዚአብሔር በመንፈስ ቅዱስ በኀይልም እንደ ቀባው፥ እየዞረም መልካም እንደ አደረገ፥ ሰይጣን ያሸነፋቸውንም እንደ ፈወሰ ታውቃላችሁ። እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበርና።
“እናንተ የእስራኤል ሰዎች ሆይ፥ ይህን ነገር ስሙ፤ እንደምታውቁት በመካከላችሁ እግዚአብሔር በእጁ ባደረገው በከሃሊነቱ በተአምራቱና በድንቅ ሥራዎቹ እግዚአብሔር የገለጠላችሁን ሰው የናዝሬቱን ኢየሱስን ስሙ።
ሐሜተኞች፥ እግዚአብሔርን የሚጠሉ፥ ተሳዳቢዎች፥ ትዕቢተኞች፥ ትምክሕተኞች፥ ክፋትን የሚፈላለጉ፥ ለወላጆቻቸውም የማይታዘዙ ናቸው።
አትስገድላቸው፤ አታምልካቸውም፤ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና፤ በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኀጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፤
አመንዝሮች ሆይ! ዓለምን መውደድ ከእግዚአብሔር ጋር መጣላት እንዲሆን አታውቁምን? እንግዲህ የዓለም ወዳጅ ሊሆን የሚፈቅድ ሁሉ የእግዚአብሔር ጠላት ሆኖአል።