ኢዮብ 38:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከግርማህስ የተነሣ የሞት በሮች ተከፍተውልሃልን? የሲኦል በረኞችስ አንተን አይተው ይደነግጣሉን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሞት ደጆች ተገልጠውልሃልን? የሞትንስ ጥላ በሮች አይተሃልን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሞት በሮች ተገልጠውልሃልን? የሞትንስ ጥላ ደጆች አይተሃልን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሞትን በሮች እንድታይ ተደርገሃልን? የድቅድቅ ጨለማንስ መዝጊያ አይተሃልን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሞት በሮች ተገልጠውልሃልን? የሞትንስ ጥላ ደጆች አይተሃልን? |
ሁሉን የሚሠራና የሚያቅናና፥ ብርሃኑን ወደ መስዕ የሚመልሰው፥ ቀኑን እንደ ሌሊት የሚያጨልመው፥ የባሕሩንም ውኃ ጠርቶ በምድር ፊት የሚያፈስሰው ስሙ ሁሉን የሚችል ጌታ እግዚአብሔር ነው።