ኢዮብ 15:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለኃጥኣን ሁሉ ሞት ምስክራቸው ነው፥ እሳት የጉቦ ተቀባዮችን ቤት ይበላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዐመፀኞች ጉባኤ ትመክናለች፤ የጉቦ ሱሰኞችም ድንኳን በእሳት ትበላለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአምላክ አልባ ሰው ጉባኤ ፍሬ የለውም፥ የጉቦ ድንኳኖችንም እሳት ትበላለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የእግዚአብሔርን ሕልውና የሚክዱ ሰዎች ዘር አይወጣላቸውም፤ በጉቦ የተሠሩ ቤቶችም በእሳት ይጋያሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዝንጉዎች ጉባኤ ሁሉ ለጥፋት ይሆናል፥ የጉቦ ተቀባዮችንም ድንኳን እሳት ትበላለች። |
እነሆኝ፥ በእግዚአብሔርና እርሱ በቀባው ፊት መስክሩብኝ፤ የማንን በሬ ወሰድሁ? የማንንስ አህያ ወሰድሁ? ማንንስ ሸነገልሁ? በማንስ ላይ ግፍ አደረግሁ? ነጠላ ጫማ እንኳን ቢሆን ከማን እጅ መማለጃ ተቀበልሁ? መስክሩብኝ፤ እኔ እመልስላችኋለሁ።”