ኤርምያስ 43:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቃርሔም ልጅ ዮሐናን፥ የጭፍራ አለቆችም ሁሉ በይሁዳ ምድር ለመቀመጥ ከተሰደዱባቸው ከአሕዛብ ሁሉ የተመለሱትን የይሁዳን ቅሬታ ሁሉ ወሰዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን፣ የቃሬያ ልጅ ዮሐናንና የጦር መኰንኖቹ ሁሉ፣ በይሁዳ ምድር ለመቀመጥ ከተበተኑበት ከአሕዛብ ሁሉ መካከል የተመለሱትን የይሁዳን ቅሬታዎች ሁሉ ይዘው ሄዱ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቃሬያም ልጅ ዮሐናን የጭፍራ አለቆችም ሁሉ በይሁዳ ምድር ለመቀመጥ ከተሰደዱባቸው ከአሕዛብ ስፍራዎች ሁሉ የተመለሱትን የይሁዳን ትሩፍ ሁሉ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ ዮሐናንና የሠራዊት አለቆች በይሁዳ የተረፉትን በሙሉ ወደ ግብጽ ወሰዱ፤ ይኸውም ከዚህ በፊት በአሕዛብ መካከል ተበታትነው ከቈዩ በኋላ እንደገና ወደ ይሁዳ አገር ተመልሰው የነበሩትን ሕዝብ ማለትም፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቃሬያም ልጅ ዮሐናን የጭፍራ አለቆችም ሁሉ በይሁዳ ምድር ለመቀመጥ ከተሰደዱባቸው ከአሕዛብ ሁሉ የተመለሱትን የይሁዳን ቅሬታ ሁሉ፥ |
እነሆ እኔም ወደ እኛ በሚመጡት ከለዳውያን ፊት እቆም ዘንድ በመሴፋ እኖራለሁ፤ እናንተ ግን ወይኑንና ፍሬውን፥ ዘይቱንም አከማቹ፤ በየዕቃችሁም ውስጥ ክተቱ፤ በያዛችኋቸውም ከተሞቻችሁ ተቀመጡ።”
እስማኤልም በመሴፋ የነበረውን የሕዝቡን ቅሬታ ሁሉ፥ የንጉሡን ሴቶች ልጆች፥ የአዛዦች አለቃ ናቡዛርዳን ለአኪቃም ልጅ ለጎዶልያስ የሰጠውን በመሴፋ የቀሩትን ሕዝብ ሁሉ መለሰ፤ የናታንያም ልጅ እስማኤል ወደ አሞን ልጆች ይሄድ ዘንድ ተነሣ።
አሁንም ጌታዬ ንጉሥ ሆይ! የእኔን የአገልጋይህን ቃል ስማ፤ እግዚአብሔር በእኔ ላይ አስነሥቶህ እንደሆነ፥ ቍርባንህን ይቀበል፤ የሰው ልጆች ግን ቢሆኑ፦ ሂድ ሌሎችን አማልክት አምልክ ብለው በእግዚአብሔር ርስት ላይ እንዳልቀመጥ ዛሬ ጥለውኛልና በእግዚአብሔር ፊት ርጉማን ይሁኑ።