ኤርምያስ 19:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤርምያስም እግዚአብሔር ትንቢት ሊናገር ወደዚያ ልኮት ከነበረው ስፍራ ከቶፌት ተመለሰ፤ በእግዚአብሔርም ቤት አደባባይ ቆሞ ለሕዝቡ ሁሉ እንዲህ አላቸው፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኤርምያስም እግዚአብሔር ትንቢት እንዲናገር ልኮት ከነበረበት ከቶፌት ተመልሶ፣ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አደባባይ በመቆም፣ ለሕዝቡ ሁሉ እንዲህ አለ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤርምያስም ጌታ ትንቢት እንዲናገር ልኮት ከነበረበት ስፍራ ከቶፌት መጣ፥ በጌታም ቤት አደባባይ ቆሞ ለሕዝብ ሁሉ እንዲህ አለ፦ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ቃሉን እንድናገርበት ካዘዘኝ ከቶፌት ተመልሼ መጣሁ፤ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አደባባይም ቆሜ እንዲህ ብዬ ነገርኳቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኤርምያስም እግዚአብሔር ትንቢት ሊናገር ወደዚያ ልኮት ከነበረው ስፍራ ከቶፌት መጣ፥ በእግዚአብሔርም ቤት አደባባይ ቆሞ ለሕዝብ ሁሉ፦ |
እግዚአብሔር እንዲህ ይለኛል፥ “ሂድ፤ የይሁዳም ነገሥታት በሚገቡበትና በሚወጡበት በሕዝብህ ልጆች በር በኢየሩሳሌምም በሮች ሁሉ ቁም።”
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “በእግዚአብሔር ቤት አደባባይ ቁም፤ በእግዚአብሔርም ቤት ውስጥ ይሰግዱ ዘንድ ለሚመጡት ለይሁዳ ከተሞች ሁሉ ትነግራቸው ዘንድ ያዘዝሁህን ቃል ሁሉ ተናገራቸው፤ አንዲትም ቃል አታጕድል።