La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 14:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አቤቱ በአ​ንተ ላይ ኀጢ​አ​ትን ሠር​ተ​ና​ልና ክፋ​ታ​ች​ን​ንና የአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ንን በደል እና​ው​ቃ​ለን።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔር ሆይ፤ ክፋታችንን ዐውቀናልና፤ የአባቶቻችንን በደል ተረድተናልና፤ በርግጥም በአንተ ላይ ኀጢአት ሠርተናል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አቤቱ! በአንተ ላይ ኃጢአትን ሠርተናልና ክፋታችንንና የአባቶቻችንን በደል እናውቃለን።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔር ሆይ! እኛ አንተን በድለናል፤ ስለዚህም የራሳችንንና የቀድሞ አባቶቻችንን ኃጢአት በፊትህ እንናዘዛለን።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አቤቱ፥ በአንተ ላይ ኃጢአትን ሠርተናልና ክፋታችንንና የአባቶቻችንን በደል እናውቃለን።

Ver Capítulo



ኤርምያስ 14:20
21 Referencias Cruzadas  

ዳዊ​ትም ናታ​ንን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በድ​ያ​ለሁ” አለው። ናታ​ንም ዳዊ​ትን አለው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደግሞ ኀጢ​አ​ት​ህን አር​ቆ​ል​ሃል፤ አት​ሞ​ት​ምም።


ሕዝ​ቡ​ንም ከቈ​ጠረ በኋላ ዳዊ​ትን ልቡ መታው፤ ዳዊ​ትም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን፥ “ባደ​ረ​ግ​ሁት ነገር እጅግ በድ​ያ​ለሁ፤ አሁን ግን አቤቱ! ታላቅ ስን​ፍና አድ​ር​ጌ​አ​ለ​ሁና የባ​ሪ​ያ​ህን ኀጢ​አት ታርቅ ዘንድ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ” አለው።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከባ​ዕድ ሕዝብ ሁሉ ራሳ​ቸ​ውን ለዩ፤ ቆመ​ውም ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንና የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ኀጢ​አት ተና​ዘዙ።


ያን​ጊ​ዜም ሰው ራሱን ይነ​ቅ​ፋል፤ እን​ዲ​ህም ይላል፦ ‘እኔ ምን አድ​ር​ጌ​አ​ለሁ? እንደ ኀጢ​አ​ቶ​ችም መጠን አል​ቀ​ጣ​ኝም፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽድ​ቅ​ንና ምጽ​ዋ​ትን ይወ​ድ​ዳል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይቅ​ር​ታው ምድ​ርን ሞላ።


አቤቱ! ኀጢ​አ​ታ​ችን ብዙ ነውና፥ በአ​ን​ተም ላይ ኀጢ​አት ሠር​ተ​ና​ልና ኀጢ​አ​ታ​ችን ተቃ​ው​ሞ​ናል፤ ነገር ግን ስለ ስምህ ብለህ አድ​ርግ።


በአ​ም​ላ​ክሽ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ እን​ዳ​መ​ፅሽ፥ መን​ገ​ድ​ሽ​ንም ከለ​መ​ለመ ዛፍ ሁሉ በታች ለእ​ን​ግ​ዶች እንደ ዘረ​ጋሽ፥ ቃሌ​ንም እን​ዳ​ል​ሰ​ማሽ ኀጢ​አ​ት​ሽን ብቻ ዕወቂ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ከት​ን​ሽ​ነ​ታ​ችን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እኛና አባ​ቶ​ቻ​ችን በአ​ም​ላ​ካ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ኀጢ​አት ሠር​ተ​ና​ልና፥ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ን​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል አል​ሰ​ማ​ን​ምና በእ​ፍ​ረ​ታ​ችን ተኝ​ተ​ናል፤ ውር​ደ​ታ​ች​ንም ሸፍ​ኖ​ናል።”


“ዝም ብለን ለምን እን​ቀ​መ​ጣ​ለን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስለ በደ​ልን አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አጥ​ፍ​ቶ​ና​ልና፥ የሐ​ሞ​ት​ንም ውኃ አጠ​ጥ​ቶ​ና​ልና ተሰ​ብ​ስ​ባ​ችሁ ወደ ተመ​ሸጉ ከተ​ሞች እን​ግባ በዚ​ያም እን​ጥፋ።


ሬስ። አቤቱ! ተጨ​ን​ቄ​አ​ለ​ሁና፥ አን​ጀ​ቴም ታው​ኮ​ብ​ኛ​ልና ተመ​ል​ከት፤ መራራ ኀዘን አዝ​ኛ​ለ​ሁና ልቤ በው​ስጤ ተገ​ላ​በ​ጠ​ብኝ፤ በሜዳ ሰይፍ አመ​ከ​ነ​ችኝ፤ በቤ​ትም ሞት አለ።


በድ​ለ​ናል፤ ዐም​ፀ​ና​ልም፤ አን​ተም አል​ራ​ራ​ህ​ል​ንም።


አባ​ቶ​ቻ​ችን ኀጢ​አ​ትን ሠሩ፤ ዛሬም የሉም፤ እኛም በደ​ላ​ቸ​ውን ተሸ​ከ​ምን።


የም​ድ​ሩ​ንም ሣር በልቶ ይጨ​ር​ሳል፤ እኔም፥ “ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ! ይቅር እን​ድ​ትል እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ፤ ያዕ​ቆ​ብን ማን ያነ​ሣ​ዋል? ጥቂት ነውና” አልሁ።