ለንጉሡም ከኪራም መርከቦች ጋር በባሕር ውስጥ የተርሴስ መርከቦች ነበሩት፤ በየሦስት ዓመትም አንድ መርከብ ከተርሴስ ወርቅና ብር፥ የተቀረጸና የተደረደረ ዕንቍ ይዞ ይመጣ ነበር።
ኤርምያስ 10:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሠራተኛና የአንጥረኛ እጅ ሥራ የሆነ ከተርሴስ ጥፍጥፍ ብር፥ ከአፌዝም ወርቅ ይመጣል፤ ልብሳቸውም ሰማያዊና ቀይ ግምጃ ነው፤ ሁሉም የብልሃተኞች ሥራ ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የተጠፈጠፈ ብር ከተርሴስ፣ ወርቅም ከአፌዝ ይመጣል። የእጅ ጥበብ ባለሙያና አንጥረኛው የሠሯቸው፣ ብልኀተኞችም ያበጇቸው ሁሉ፣ ሰማያዊና ሐምራዊ ልብስ ተጐናጽፈዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሞያተኛና የአንጥረኛ እጅ ሥራ የሆነ ከተርሴስ ጥፍጥፍ ብር ከአፌዝም ወርቅ ይመጣል፤ ልብሳቸውም ሰማያዊና ሐምራዊ ነው፥ ሁሉም የብልሃተኞች ሥራ ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምስሎቻቸው ከተርሴስ በመጣ ጥሬ ብርና ከኡፋዝ በተገኘ ወርቅ ተለብጠዋል፤ በብልኀተኞችም ሥራ አጊጠዋል፤ ጥበበኞች ሸማኔዎች በሠሩአቸውም የወይን ጠጅና ሐምራዊ ልብስ ተሸፍነዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሠራተኛና የአንጥረኛ እጅ ሥራ የሆነ ከተርሴስ ጥፍጥፍ ብር ከአፌዝም ወርቅ ይመጣል፥ ልብሳቸውም ሰማያዊና ቀይ ግምጃ ነው፥ ሁሉም የብልሃተኞች ሥራ ናቸው። |
ለንጉሡም ከኪራም መርከቦች ጋር በባሕር ውስጥ የተርሴስ መርከቦች ነበሩት፤ በየሦስት ዓመትም አንድ መርከብ ከተርሴስ ወርቅና ብር፥ የተቀረጸና የተደረደረ ዕንቍ ይዞ ይመጣ ነበር።
ለንጉሡም ከኪራም አገልጋዮች ጋር ወደ ተርሴስ የሚሄዱ መርከቦች ነበሩት፤ በሦስት በሦስት ዓመትም አንድ ጊዜ የተርሴስ መርከቦች ወርቅና ብር፥ የዝሆንም ጥርስና ዝንጀሮ ይዘው ይመጡ ነበር።
“ከኀይልሽ ሁሉ ብዛት የተነሣ የተርሴስ ሰዎች ነጋዴዎችሽ ነበሩ፤ ገበያሽን ብር፥ ወርቅና ብረት፥ ቆርቆሮና እርሳስም አደረጉ።
ዓላማ እንዲሆንልሽ ሸራሽ ከግብፅ በፍታና ከወርቀ ዘቦ ተሠርቶአል፤ መደረቢያሽም ከኤሊሳ ደሴቶች ሰማያዊና ቀይ ሐር ተሠርቶአል።
ይህ ደግሞ በእስራኤል ዘንድ ነው፤ ሠራተኛ ሠራው፤ እርሱም አምላክ አይደለም፤ ሰማርያ ሆይ! እንቦሳሽ ተቅበዝብዞአልና።
ዮናስ ግን ከእግዚአብሔር ፊት ወደ ተርሴስ ይሸሽ ዘንድ ተነሣ፤ ወደ ኢዮጴም ወረደ፤ ወደ ተርሴስም የምታልፍ መርከብ አገኘ፤ ከእግዚአብሔርም ፊት ኰብልሎ ከእነርሱ ጋር ወደ ተርሴስ ይሄድ ዘንድ ዋጋ ሰጥቶ ወደ እርስዋ ገባ።
እንጨቱን፦ ንቃ፥ ዲዳውንም ድንጋይ፦ ተነሣ ለሚለው ወዮለት! በውኑ ይህ ያስተምራልን? እነሆ፥ በወርቅና በብር ተለብጦአል፥ ምንም እስትንፋስ የለበትም።