ያዕቆብ 2:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተ ግን ድኾችን አዋረዳችሁ። ባለ ጠጎቹ የሚያስጨንቁአችሁ አይደሉምን? ወደ ፍርድ ቤትም የሚጎትቱአችሁ እነርሱ አይደሉምን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተ ግን ድኾችን አዋረዳችሁ፤ እናንተን የሚያስጨንቋችሁ ሀብታሞች አይደሉምን? ወደ ፍርድ ቤት የሚጐትቷችሁስ እነርሱ አይደሉምን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተ ግን ድኾችን አዋረዳችሁ፤ እናንተን የሚያስጨንቋችሁ ሀብታሞች አይደሉምን? ወደ ፍርድ ቤት የሚጐትቷችሁስ እነርሱ አይደሉምን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ ግን ድኾችን ትንቃላችሁ፤ የሚጨቊኑአችሁና ወደ ፍርድ ቤት የሚጐትቷችሁስ ሀብታሞች አይደሉምን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተ ግን ድሆችን አዋረዳችሁ። ባለ ጠጎቹ የሚያስጨንቁአችሁ አይደሉምን? ወደ ፍርድ ቤትም የሚጎትቱአችሁ እነርሱ አይደሉምን? |
ኀጢአተኞች እነሆ፥ ቀስታቸውን ገትረዋልና፥ ፍላጻቸውንም በአውታር አዘጋጅተዋልና፥ ልበ ቅኖቹን በስውር ይነድፉ ዘንድ።
ከፍ ካለው በላይ ከፍ ያለ ይጠብቅሃልና፥ ከእነርሱም በላይ ደግሞ ሌሎች ከፍ ይላሉና በሀገሩ ድሃ ሲበደል፥ ፍርድና ጽድቅም ሲነጠቅ ብታይ በሥራው አታድንቅ።
መልኩም የተናቀ፥ ከሰውም ልጆች ሁሉ የተዋረደ፥ የተገረፈ ሰው፥ መከራንም የተቀበለ ነው፤ ፊቱንም መልሶአልና አቃለሉት፥ አላከበሩትምም።
በሰማርያ ተራራ የምትኖሩ፥ ድሆችንም የምትበድሉ፥ ችግረኞችንም የምታስጨንቁ፥ ጌቶቻቸውንም፦ አምጡ እንጠጣ የምትሉ እናንተ የባሳን ላሞች ሆይ! ይህን ቃል ስሙ።
ድሃውንም ደብድባችኋልና፤ መማለጃንም ከእርሱ ወስዳችኋልና፤ ያማሩ ቤቶችንም መርጣችሁ ሠርታችኋልና፥ ነገር ግን አትኖሩባቸውም፤ ያማሩ የወይን ቦታዎችም ተክላችኋል፤ ነገር ግን ወይንን አትጠጡም።
ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፥ “እኔ አባቴን አከብራለሁ እንጂ ጋኔን የለብኝም፤ እናንተ ግን ትንቁኛላችሁ።
አይሁድ ግን እግዚአብሔርን የሚፈሩ የከበሩ ሴቶችንና የከተማውን ሽማግሌዎች አነሳሡአቸው፤ በጳውሎስና በበርናባስ ላይም ስደትን አስነሡ፤ ከሀገራቸውም አባረሩአቸው።
በአጧቸውም ጊዜ ኢያሶንን ጐተቱት፤ በዚያም የነበሩትን ጓደኞች ጭምር ወደ ሹሞቹ ወሰዱአቸው፤ እየጮኹም እንዲህ ይሉ ነበር፥ “ዓለምን የሚያውኳት እነዚህ ናቸው፤ ወደዚህም መጥተዋል።
ሳውል ግን ገና አብያተ ክርስቲያናትን ይቃወም ነበር፤ የሰውንም ቤት ሁሉ ይበረብር ነበር፤ ወንዶችንም ሴቶችንም እየጐተተ ወደ ወኅኒ ቤት ያስገባቸው ነበር።
በውኑ የምትበሉበትና የምትጠጡበት ቤት የላችሁምን? ወይስ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ታስነቅፋላችሁን? ነዳያንንስ ታሳፍሩአቸዋላችሁን? ምን እላለሁ? በዚህ አመሰግናችኋለሁን? አላመሰግናችሁም።
የጌጥ ልብስም የለበሰውን ተመልክታችሁ “አንተስ በዚህ በመልካም ስፍራ ተቀመጥ፤” ብትሉት፥ ድኻውንም “አንተስ ወደዚያ ቁም” ወይም “ከእግሬ መረገጫ በታች ተቀመጥ፤” ብትሉት፥ ራሳችሁን መለያየታችሁ አይደለምን?