በእስራኤልም ንጉሥ በፋቁሔ ዘመን የአሶር ንጉሥ ቴልጌልቴልፌልሶር መጣ፤ ኢዮንና አቤልቤትመዓካን፥ ያኖዋንም፥ ቃዴስንና አሶርንም፥ ገለዓድንና ገሊላንም፥ የንፍታሌምንም ሀገር ሁሉ ወሰደ፤ ወደ አሶርም አፈለሳቸው።
ኢሳይያስ 9:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ እግዚአብሔር በጽዮን ተራራ ላይ እርሱን በመቃወም የሚነሡትን ይበትናቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን እግዚአብሔር የረአሶንን ጠላቶች አጠንክሯል፤ በርሱም ላይ ባላጋራዎቹን ያነሣሣበታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሶርያውያን ከምሥራቅ፤ ፍልስጥኤማውያን ከምዕራብ፤ አፋቸውን ከፍተው እስራኤልን ይቦጫጭቋታል። ይህም ሁሉ ሆኖ፤ ቁጣው ገና አልበረደም፤ እጁ እንደ ተዘረጋ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ እግዚአብሔር ተቀናቃኞችን በእነርሱ ላይ ያስነሣባቸዋል፤ ጠላቶቻቸውንም በእነርሱ ላይ ያነሣሣባቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ እግዚአብሔር በጽዮን ተራራ ላይ ተቋቋሚ ያስነሳበታል፥ |
በእስራኤልም ንጉሥ በፋቁሔ ዘመን የአሶር ንጉሥ ቴልጌልቴልፌልሶር መጣ፤ ኢዮንና አቤልቤትመዓካን፥ ያኖዋንም፥ ቃዴስንና አሶርንም፥ ገለዓድንና ገሊላንም፥ የንፍታሌምንም ሀገር ሁሉ ወሰደ፤ ወደ አሶርም አፈለሳቸው።
የአሦርም ንጉሥ ሰማው፤ የአሦርም ንጉሥ ወደ ደማስቆ ወጣ፤ ያዛትም፤ ሕዝብዋንም ወደ ቂር አፈለሳቸው፤ ረአሶንንም ገደለው።
በሐሣር እንዳትወድቁ፥ ክብራችሁን ወዴት ትተዉታላችሁ? በዚህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አልተመለሰችም፤ ነገር ግን እጁ ገና ተዘርግታ ትኖራለች።
ለኤፍሬም ምንደኞች ትዕቢት አክሊል፥ ያለ ወይን ጠጅ ለሰከሩ፥ በወፍራም ተራራ ራስ ላይ ላለችም ለረገፈች ለክብር ጌጥ አበባ ወዮ!
ስለዚህ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ ታላቅ ቍጣን ተቈጣ፤ እጁንም በላያቸው ዘርግቶ መትቶአቸዋል፤ ተራሮችም ተንቀጠቀጡ፤ ሬሳቸውም በመንገድ መካከል እንደ ጕድፍ ሆኖአል። በዚህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አልተመለሰችም፤ ነገር ግን እጁ ገና ተዘርግታ ትኖራለች።
እንዲህም ሆነ፤ በይሁዳ ንጉሥ በዖዝያን ልጅ በኢዮአታም ልጅ በአካዝ ዘመን የአራም ንጉሥ ረአሶን፥ የእስራኤልም ንጉሥ የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ ኢየሩሳሌምን ሊወጉ ወጡ፤ ሊይዙአትም አልቻሉም።
የአራም ራስ ደማስቆ ነው፤ የደማስቆም ራስ ረአሶን ነው፤ በስድሳ አምስት ዓመት ውስጥ የኤፍሬም መንግሥት ከሕዝብ ይጠፋል፤