ርብቃም ይስሐቅን አለችው፥ “ከኬጢ ሴቶች ልጆች የተነሣ ሕይወቴን ጠላሁት፤ ያዕቆብ ከዚህ ሀገር ሴቶች ልጆች ሚስትን የሚያገባ ከሆነ በሕይወት መኖር ለእኔ ምኔ ነው?”
ኢሳይያስ 15:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሐሴቦንና ኤልያሊ ጮኹ፤ ድምፃቸውም እስከ ያሳ ድረስ ይሰማል፤ ስለዚህ የሞዓብ ወገብ ይታመማል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሐሴቦንና ኤልያሊ ጮኹ፤ ድምፃቸው እስከ ያሀጽ ድረስ ተሰማ፤ ስለዚህ የሞዓብ ጦረኞች ጮኹ፤ ልባቸውም ራደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሐሴቦንና ኤልያሊ ጮሁ፥ ድምፃቸው እስከ ያሀፅ ድረስ ተሰማ፤ ስለዚህ የሞዓብ ሰልፈኞች ጮኹ፤ ነፍሱም ራደች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሐሴቦንና የኤልዓሌ ሕዝቦች ይጮኻሉ፤ የጩኸታቸውም ድምፅ እስከ ያሐጽ ድረስ ይሰማል፥ የሞአብ ወታደሮች ሳይቀሩ ወኔያቸው ከድቶአቸው በፍርሃት ተርበደበዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሐሴቦንና ኤልያሊ ጮሁ ድምፃቸው እስከ ያሀፅ ድረስ ይሰማል፥ ስለዚህ የሞዓብ ሰልፈኞች ጮኹ፥ ነፍስዋ በውስጥዋ ተንቀጠቀጠች። |
ርብቃም ይስሐቅን አለችው፥ “ከኬጢ ሴቶች ልጆች የተነሣ ሕይወቴን ጠላሁት፤ ያዕቆብ ከዚህ ሀገር ሴቶች ልጆች ሚስትን የሚያገባ ከሆነ በሕይወት መኖር ለእኔ ምኔ ነው?”
እርሱም አንድ ቀን የሚያህል መንገድ በምድረ በዳ ሄደ፤ መጥቶም ከደድሆ ዛፍ በታች ተቀመጠና፦ ይበቃኛል፤ አሁንም አቤቱ! እኔ ከአባቶቼ አልበልጥምና ነፍሴን ውሰድ” ብሎ እንዲሞት ለመነ።
ከሐሴቦን ጩኸት እስከ ኤሊያሊና እስከ ኢያሳ ድረስ ድምፃቸውን ሰጥተዋል፤ ከሴጎር እስከ ሖሮናይምና እስከ ዔግላት ሺሊሺያ ድረስ ይደርሳል፤ የኔምሬም ውኃ ደርቋልና።
ፀሐይም በወጣች ጊዜ እግዚአብሔር ትኩስ የምሥራቅ ነፋስን አዘዘ፤ ዮናስንም እስኪዝል ድረስ ፀሐይ ራሱን መታው፤ ለራሱም ተስፋ ቈርጦ፥ “ከሕይወት ሞት ይሻለኛል” አለ።
እንዲህስ ከምታደርግብኝ፥ በፊትህ ይቅርታን አግኝቼ እንደ ሆነ፥ በእኔ ላይ የሚሆነውን መከራ እንዳላይ፥ እባክህ፥ ፈጽሞ ግደለኝ።”
ሴዎንም እስራኤል በወሰኑ ላይ ያልፉ ዘንድ አልፈቀደም፤ ሴዎንም ሕዝቡን ሁሉ ሰበሰበ፤ እስራኤልንም ለመውጋት ወደ ምድረ በዳ ወጣ፤ ወደ ኢያሶንም መጣ፤ እስራኤልንም ተዋጋቸው።
ሴዎንም እስራኤል በድንበሩ እንዲያልፍ እንቢ አለ፤ ነገር ግን ሴዎን ሕዝቡን ሁሉ ሰበሰበ፤ በኢያሴርም ሰፈረ፤ ከእስራኤልም ጋር ተዋጋ።