በዚያችም ሌሊት የእግዚአብሔር መልአክ መጣ፤ ከአሦራውያንም ሰፈር መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ገደለ፤ ማለዳም በተነሡ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሁሉ በድኖች ነበሩ።
ኢሳይያስ 10:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ምድያምን በመከራው ቦታ እንደ መታው ጅራፍን ያነሣበታል፤ ቍጣውም በባሕሩ መንገድና በግብፅ መንገድ በኩል ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ምድያምን በሔሬብ ዐለት አካባቢ እንደ መታ፣ በጅራፍ ይገርፋቸዋል፤ በግብጽ እንዳደረገውም ሁሉ፣ በትሩን በውሆች ላይ ያነሣል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ምድያምን በሔሬብ ዐለት አካባቢ እንደ መታ፤ በጅራፍ ይገርፋቸዋል፤ በግብጽ እንዳደረገውም ሁሉ፤ በትሩን በውሆች ላይ ያነሣል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ የሠራዊት አምላክ በዖሬብ አለት አጠገብ በምድያማውያን ላይ እንዳደረግሁት አሦራውያንን የምቀጣበት ጅራፍ ባሕሩን በበትሬ መትቼ ግብጻውያንን እንደቀጣሁ አሦራውያንን እቀጣለሁ። በግብጽ ላይ በትሬን እንዳነሣሁ በኤፍራጥስ ወንዝ ላይም አነሣለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም ምድያምን በሔሬብ ዓለት በኩል እንደ መታው ጅራፍ ያነሣበታል፥ በትሩም በባሕር ላይ ይሆናል፥ በግብፅም እንዳደረገ ያነሣዋል። |
በዚያችም ሌሊት የእግዚአብሔር መልአክ መጣ፤ ከአሦራውያንም ሰፈር መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ገደለ፤ ማለዳም በተነሡ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሁሉ በድኖች ነበሩ።
እግዚአብሔር አምላክ ምጽዋትንና እውነትን ይወድዳልና፥ እግዚአብሔር ክብርና ሞገስን ይሰጣል፤ እግዚአብሔር በቅንነት የሚሄዱትን ከበረከቱ አያሳጣቸውም።
አንተም በትርህን አንሣ፤ እጅህንም በባሕሩ ላይ ዘርጋ፤ ክፈለውም፤ የእስራኤልም ልጆች በባሕሩ ውስጥ በየብስ ያልፋሉ።
ስለዚህ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “በጽዮን የምትኖር ሕዝቤ ሆይ፥ ከአሦር የተነሣ አትፍራ፤ በበትር ይመቱሃልና፥ የግብፅንም መንገድ ታይ ዘንድ መቅሠፍቴን አመጣብሃለሁና።
እግዚአብሔርም የድምፁን ክብር ያሰማል፤ የክንዱንም መፈራት፥ በጽኑ ቍጣና በምትበላ እሳት፥ በወጀብም፥ በዐውሎ ነፋስም፥ በበረዶም ድንጋይ ይገልጣል።
እግዚአብሔር በላዩ የሚያወርድበት የታዘዘበቱ የበትር ድብደባ ሁሉ በከበሮና በመሰንቆ ይሆናል፤ በጦርነትም ክንዱን አንሥቶ ይዋጋቸዋል።
በምድያም ጊዜ እንደ ሆነ በላያቸው የነበረው ቀንበር ተነሥቶአልና፥ በጫንቃቸው የነበረውንም፥ የአስጨናቂዎችንም በትር መልሶአልና።
አሕዛብም ተቈጡ፤ ቍጣህም መጣ፤ በሙታንም ትፈርድ ዘንድ ዘመን መጣ፤ ለባሪያዎችህም ለነቢያትና ለቅዱሳን ስምህንም ለሚፈሩት ለታናናሾችና ለታላላቆችም ዋጋቸውን ትሰጥ ዘንድ፥ ምድርንም የሚያጠፉትን ታጠፋ ዘንድ ዘመን መጣ።”
አሕዛብንም ይመታበት ዘንድ ስለታም ሰይፍ ከአፉ ይወጣል፤ እርሱም በብረት በትር ይገዛቸዋል፤ እርሱም ሁሉን የሚገዛ የእግዚአብሔርን የብርቱ ቍጣውን ወይን መጥመቂያ ይረግጣል።
የምድያምን ሁለቱን አለቆች ሔሬብንና ዜብን ያዙ፤ ሔሬብንም በሱርኤራብ ገደሉት፥ ዜብንም በኢያፌቅ ገደሉት፤ የምድያምንም ሰዎች አሳደዱ፤ የሔሬብንና የዜብንም ራስ ይዘው ወደ ዮርዳኖስ ማዶ ወደ ጌዴዎን አመጡ።