እንዲህም ሆነ፤ በሦስተኛው ቀን ፈርዖን የተወለደበት ዕለት ነበር፤ ለሠራዊቱም ሁሉ ግብር አደረገ፤ የጠጅ አሳላፊዎቹን አለቃና የእንጀራ አበዛዎቹን አለቃ በአሽከሮቹ መካከል ዐሰበ።
ሆሴዕ 7:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በንጉሦቻችን ቀን አለቆች ከወይን ጠጅ ሙቀት የተነሣ ታመሙ፤ እነርሱም ከዋዘኞች ጋር እጆቻቸውን ዘረጉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በንጉሣችን የበዓል ቀን፣ አለቆች በወይን ጠጅ ስካር ጋሉ፤ እርሱም ከፌዘኞች ጋራ ተባበረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በንጉሣችን ቀን ሹማምንቱ ከወይን ጠጅ ሞቅታ የተነሣ ታመሙ፤ እርሱም ከፌዘኞች ጋር እጁን ዘረጋ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በንጉሣቸው ክብረ በዓል ቀን መኳንንቱ ብዙ የወይን ጠጅ በመጠጣት ሰክረው ታመሙ፤ ጋጋሪውም ለሚያፌዙ ሰዎች ምልክት ለመስጠት እጁን ዘረጋ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በንጉሣችን ቀን አለቆች ከወይን ጠጅ ሙቀት የተነሣ ታመሙ፥ እርሱም ከዋዘኞች ጋር እጁን ዘረጋ። |
እንዲህም ሆነ፤ በሦስተኛው ቀን ፈርዖን የተወለደበት ዕለት ነበር፤ ለሠራዊቱም ሁሉ ግብር አደረገ፤ የጠጅ አሳላፊዎቹን አለቃና የእንጀራ አበዛዎቹን አለቃ በአሽከሮቹ መካከል ዐሰበ።
ከዚህም በኋላ ንጉሡ ኢዮርብዓም የእግዚአብሔር ሰው በቤቴል ባለው መሠዊያ ላይ የተናገረውን ነገር በሰማ ጊዜ፥ ንጉሡ፥ “ያዙት” ብሎ እጁን ከመሠዊያው ላይ አነሣ። ከዚህም በኋላ በእርሱ ላይ የዘረጋት እጁ ደረቀች፤ ወደ እርሱም ይመልሳት ዘንድ አልተቻለውም።
ምስጉን ነው፥ በዝንጉዎች ምክር ያልሄደ፥ በኀጢአተኞችም መንገድ ያልቆመ፥ በዋዘኞችም ወንበር ያልተቀመጠ ሰው።
ለኤፍሬም ምንደኞች ትዕቢት አክሊል፥ ያለ ወይን ጠጅ ለሰከሩ፥ በወፍራም ተራራ ራስ ላይ ላለችም ለረገፈች ለክብር ጌጥ አበባ ወዮ!