ተነሣና ወደ እናትህ አባት ወደ ባቱኤል ቤት ወደ ሁለቱ ወንዞች መካከል ሂድ፤ ከዚያም ከእናትህ ከርብቃ ወንድም ከላባ ሴቶች ልጆች ሚስትን አግባ።
ሆሴዕ 12:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያዕቆብ ወደ ሶርያ ሀገር ሸሸ፤ እስራኤልም ስለ ሚስት አገለገለ፤ ስለ ሚስትም ጠበቀ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር በነቢይ አማካይነት እስራኤልን ከግብጽ አወጣ፤ በነቢይም በኩል ተንከባከበው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያዕቆብ ወደ አራም ምድር ሸሸ፥ እስራኤልም ስለ ሚስት አገለገለ፥ ስለ ሚስትም በጎችን ያሰማራ ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር በላከው ነቢይ አማካይነት የእስራኤልን ሕዝብ ከግብጽ መርቶ አወጣቸው፤ በዚያም ነቢይ አማካይነት ተንከባከባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያዕቆብ ወደ ሶርያ አገር ሸሸ፥ እስራኤልም ስለ ሚስት አገለገለ፥ ስለ ሚስትም ጠባቂ ነበረ። |
ተነሣና ወደ እናትህ አባት ወደ ባቱኤል ቤት ወደ ሁለቱ ወንዞች መካከል ሂድ፤ ከዚያም ከእናትህ ከርብቃ ወንድም ከላባ ሴቶች ልጆች ሚስትን አግባ።
ሙሴም ሕዝቡን አለ፥ “ከባርነት ቤት ከግብፅ የወጣችሁባትን ይህችን ቀን ዐስቡ፤ እግዚአብሔር ከዚህ ቦታ በበረታች እጅ አውጥቶአችኋልና። ስለዚህ የቦካ እንጀራ አትብሉ።
በእስራኤልም ሠራዊት ፊት ይሄድ የነበረው የእግዚአብሔር መልአክ ፈቀቅ ብሎ በኋላቸው ሄደ፤ የደመናውም ዐምድ ከፊታቸው ፈቀቅ ብሎ በኋላቸው ቆመ፤
ከዚያም የተገኘውን ገንዘብዋን እሰጣታለሁ፤ ምክርዋንም በአኮር ሸለቆ እገልጣለሁ፤ እንደ ሕፃንነትዋ ወራት፥ ከግብፅም እንደ ወጣችበት ቀን ትዘምራለች።
እኔ አፍ ለአፍ በግልጥ እናገረዋለሁ፤ በስውርም አይደለም፤ የእግዚአብሔርንም ክብር ያያል፤ አገልጋዬ ሙሴን ማማትን ስለ ምን አልፈራችሁም?” አለ።
በአምላክህም በእግዚአብሔር ፊት እንዲህ ብለህ ተናገር፦ አባቴ ከሶርያ ወጥቶ ወደ ግብፅ ወረደ፤ በዚያም በቍጥር ጥቂት ሆኖ ኖረ፤ በዚያም ታላቅና የበረታ፥ ብዙም ሕዝብ ሆነ።
ያዕቆብና ልጆቹ ወደ ግብጽ በገቡ ጊዜ ግብጻውያን አስጨነቁአቸው፤ አባቶቻችሁም ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ እግዚአብሔርም ሙሴንና አሮንን ላከ፤ አባቶቻችሁንም ከግብጽ አውጥተው በዚህ ቦታ አኖሩአቸው።