ዕንባቆም 3:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በውኑ እግዚአብሔር በወንዞች ላይ ተቈጥቶአልን? ቍጣህ በወንዞች ላይ፥ መዓትህም በባሕር ላይ ነውን? በፈረሶችህና በማዳንህ ሰረገሎች ላይ ተቀምጠሃልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ በወንዞች ላይ ተቈጣህን? መዓትህስ በምንጮች ላይ ነበርን? በፈረሶችህና በድል አድራጊ ሠረገሎችህ በጋለብህ ጊዜ፣ በባሕር ላይ ተቈጥተህ ነበርን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ሆይ ንዴትህ በወንዞች ላይ ነውን? ወይስ ቁጣህ በወንዞች ላይ ወይም መዓትህ በባሕር ላይ ነውን? በፈረሶችህ፥ በማዳን ሰረገሎች ላይ ተቀምጠሃልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሆይ! ፈረሶችህንና ሠረገላዎችህን ወደ ድል በመራኸቸው ጊዜ፥ ኀይለኛው ቊጣህ በወንዞች ላይ ነበርን? ወይስ በባሕሩ ላይ ተቈጥተህ ነበርን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በውኑ እግዚአብሔር በወንዞች ላይ ተቈጥቶአልን? ቍጣህ በወንዞች ላይ፥ መዓትህም በባሕር ላይ ነውን? በፈረሶችህና በማዳንህ ሰረገሎች ላይ ተቀምጠሃልና። |
አንተም በትርህን አንሣ፤ እጅህንም በባሕሩ ላይ ዘርጋ፤ ክፈለውም፤ የእስራኤልም ልጆች በባሕሩ ውስጥ በየብስ ያልፋሉ።
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “ወንድምህ አሮንን፦ ‘በትርህን ውሰድ፤ በግብፅ ውኆች፥ በወንዞቻቸው፥ በመስኖዎቻቸውም፥ በኩሬዎቻቸውም፥ በውኃ ማከማቻቸውም ሁሉ ላይ እጅህን ዘርጋ’ በለው፤ ደምም ይሆናል፤” በግብፅም ሀገር ሁሉ በዕንጨት ዕቃና በድንጋይ ዕቃ ሁሉ ደም ሆነ።
ሙሴና አሮንም እግዚአብሔር እንዳዘዛቸው እንዲሁ አደረጉ፤ አሮንም በትሩን አነሣ፤ በፈርዖንና በሹሞቹ ፊት የወንዙን ውኃ መታ፤ የወንዙም ውኃ ሁሉ ተለውጦ ደም ሆነ።
ስለ ግብፅ የተነገረ ራእይ። እነሆ፥ እግዚአብሔር በፈጣን ደመና ተቀምጦ ወደ ግብፅ ይመጣል፤ የግብፅም የእጆቻቸው ሥራዎች በፊቱ ይዋረዳሉ፤ የግብፃውያንም ልብ በውስጣቸው ይቀልጣል።
እነሆ፥ መጣሁ፤ ሰውም አልነበረም፤ ተጣራሁ፤ የሚመልስም አልነበረም፤ እጄ ለማዳን ጠንካራ አይደለምን? ወይስ ለማዳን አልችልምን? እነሆ፥ በገሠጽሁ ጊዜ ባሕርን አደርቃለሁ፤ ወንዞችንም ምድረ በዳ አደርጋቸዋለሁ፤ ውኃም በማጣት ዐሣዎቻቸው ይሞታሉ፤ በጥማትም ያልቃሉ።
እነሆ፥ እግዚአብሔር መዓቱን በቍጣ፥ ዘለፋውንም በእሳት ነበልባል ይመልስ ዘንድ እንደ እሳት ይመጣል፤ ሰረገሎቹም እንደ ዐውሎ ነፋስ ይሆናሉ።