ዔሳው ከከነዓን ልጆች ሚስቶችን አገባ፤ የኬጤያዊውን የዔሎን ልጅ ሐዳሶን፥ የኤውያዊው የሴቤሶ ልጅ ሐና የወለዳትን ኤሌባማን፥
ዘፍጥረት 36:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሳባቅ ልጆችም እነዚህ ናቸው፤ ኢኣ፥ ዓናን፤ ይህም ዓናን በምድረ በዳ የአባቱን የሳባቅን አህዮች ሲጠብቅ ፍል ውኃዎችን ያገኘ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የፂብዖን ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው፦ አያ እና ዓና፤ ይህ ዓና የአባቱን የፂብዖንን አህዮች ሲጠብቅ፣ የፍል ውሃ ምንጮችን በምድረ በዳ ያገኘ ሰው ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የፅብዖን ልጆችም፦ አያና ዓና ናቸው። ይህ ዓና የአባቱን የፅብዖንን አህዮች ሲጠብቅ በበረሓ ውስጥ የፍል ውሃ ምንጮችን ያገኘ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጺባዖን ልጆችም አያ እና ዐና ናቸው። ይህም ዐና የአባቱን አህዮች ሲጠብቅ በበረሓ ውስጥ የፍል ውሃ ምንጮችን ያገኘ ሰው ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አያዓና ይህም ዓና በምድረ በዳ የአባቱን የፅብዖንን አህዮች ሲጠብቅ ፍልውኆችን ያገኘ ነው። |
ዔሳው ከከነዓን ልጆች ሚስቶችን አገባ፤ የኬጤያዊውን የዔሎን ልጅ ሐዳሶን፥ የኤውያዊው የሴቤሶ ልጅ ሐና የወለዳትን ኤሌባማን፥
የአቤሴሎምም አገልጋዮች አቤሴሎም እንዳዘዛቸው በአምኖን ላይ አደረጉበት። የንጉሡም ልጆች ሁሉ ተነሥተው በየበቅሎዎቻቸው ተቀምጠው ሸሹ።
አቤሴሎምም ከዳዊት አገልጋዮች ጋር ተገናኘ፤ አቤሴሎምም በበቅሎ ተቀምጦ ነበር፤ በቅሎውም ብዙ ቅርንጫፍ ባለው በታላቅ ዛፍ በታች ገባ፤ ራሱም በዛፉ ተያዘ፤ በሰማይና በምድርም መካከል ተንጠለጠለ፤ ተቀምጦበትም የነበረው በቅሎ በበታቹ አለፈ።
ካህኑም ሳዶቅና ነቢዩ ናታን የዮዳሄም ልጅ በናያስ ከሊታውያንና ፈሊታውያንም ወረዱ፤ ሰሎሞንንም በንጉሡ በዳዊት በቅሎ ላይ አስቀምጠው ወደ ግዮን ወሰዱት።
ንጉሡም ከእርሱ ጋር ካህኑን ሳዶቅንና ነቢዩን ናታንን፥ የዮዳሄንም ልጅ በናያስን፥ ከሊታውያንንና ፈሊታውያንንም ላከ፤ በንጉሡም በቅሎ ላይ አስቀመጡት።
እያንዳንዱም እንደ ደንቡ የንጉሡን ሰረገላዎች ለሚስቡ ለፈረሶችና ለሰጋር በቅሎዎች ገብስና ገለባ፥ እንዲሁም ዕቃዎችን ወደ ስፍራቸው ያመጡ ነበር።
በሳሮንም በሚሰማሩ ከብቶች ላይ ሳሮናዊው ሰጥራይ ሹም ነበረ፤ በሸለቆዎቹም ውስጥ በነበሩት ከብቶች ላይ የዓድላይ ልጅ ሳፋጥ ሹም ነበረ፤
“ሥርዐቴን ጠብቁ፤ በበሬህ በባዕድ ቀንበር አትረስ፤ በወይን ቦታህ የተለያየ ዘር አትዝራ፤ ከሁለት ዐይነት ነገር የተሠራ ልብስ ኀፍረት ነውና አትልበስ።