አቤሜሌክም አንድ ሺህ ምዝምዝ ብርን በጎችንና ላሞችን፥ ወንዶችና ሴቶች ባሪያዎችን አመጣ፤ ለአብርሃምም ሰጠው፤ ሚስቱን ሣራንም መለሰለት።
ዘፍጥረት 21:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም በእኔም፥ በልጄም፥ በወገኔም፥ ከእኔም ጋር ባለ ክፉ እንዳታደርግብኝ በእግዚአብሔር ማልልኝ፤ ነገር ግን በእንግድነት መጥተህ ለአንተ ቸርነት እንዳደረግሁ አንተም ለእኔ፥ ለተቀምጥህባትም ምድር ቸርነትን ታደርጋለህ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ እኔንና ልጆቼን፣ ዘሬንም በመሸንገል አንዳች ክፉ ነገር እንዳታደርስብን በእግዚአብሔር ፊት ማልልኝ። እኔ ለአንተ ቸርነት እንዳደረግሁ፣ አንተም ለእኔና በእንግድነት ለተቀመጥህባት ለዚህች ምድር ቸርነት አድርግ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁንም በእኔም በልጄም በልጅ ልጄም ክፉ እንዳታደርግብኝ በእግዚአብሔር ማልልኝ፥ ነገር ግን ለአንተ ቸርነትን እንዳደረግሁ አንተም ለእኔ ለተቀመጥህባትም ምድር ቸርነትን ታደርጋለህ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔንም ሆነ ልጆቼን ወይም ዘሮቼን በማታለል እንዳትበድል እዚህ በእግዚአብሔር ስም ማልልኝ፤ እኔ ለአንተ ታማኝነትን አሳይቻለሁ፤ አንተም ለእኔና ለዚህች በመጻተኛነት ለምትኖርባት አገር ታማኝነትን እንደምታሳይ ማልልኝ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁንም በእኔም በልጄም በልጅ ልጄም ክፉ እንዳታደርግብኝ በእግዚአብሔር ማልልኝ፤ ነገር ግን ለአንተ ቸርነትን እንዳደረግሁ አንተም ለእኔ ለተቀመጥህባትም ምድር ቸርነትን ታደርጋለህ። |
አቤሜሌክም አንድ ሺህ ምዝምዝ ብርን በጎችንና ላሞችን፥ ወንዶችና ሴቶች ባሪያዎችን አመጣ፤ ለአብርሃምም ሰጠው፤ ሚስቱን ሣራንም መለሰለት።
“እጅህን በእጄ ላይ አድርግ፤ እኔም አብሬ ከምኖራቸው ከከነዓን ሴቶች ልጆች ለልጄ ለይስሐቅ ሚስት እንዳትወስድለት በሰማይና በምድር አምላክ በእግዚአብሔር አምልሃለሁ፤
እነርሱም አሉት፥ “እኛ የጠላንህ አይደለም፤ በመልካም አኑረን፥ በመልካም አሰናበትንህ እንጂ፥ አሁንም አንተ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ቡሩክ ነህ።
አንተም ወደ እኔ ብታልፍ የአብርሃም አምላክ የናኮርም አምላክ በእኛ መካከል ይፍረድ።” ያዕቆብም በአባቱ በይስሐቅ አምላክ ማለ።
ጌታውም እግዚአብሔር ከዮሴፍ ጋር እንዳለ፥ እርሱ የሚሠራውንም ሁሉ እግዚአብሔር በእጁ እንዲያከናውንለት አየ።
ሕያው እግዚአብሔርን! ብሎ በእውነትና በቅንነት፤ በጽድቅም ቢምል፥ አሕዛብ በእርሱ ይባረካሉ፤ በኢየሩሳሌምም እግዚአብሔርን ያመሰግናሉ።
አሁንም፥ በእግዚአብሔር ማሉልኝ፤ እኔ ለእናንተ ቸርነት እንደ አደረግሁ እናንተ ደግሞ ለአባቴ ቤት ቸርነት እንድታደርጉ፥ በእውነት ምልክት ስጡኝ።
አባቴም በአንተ ላይ ክፋት ማድረግ ቢወድድ፥ እኔም ባላስታውቅህ፥ በሰላምም ትሄድ ዘንድ ባላሰናብትህ፥ እግዚአብሔር በዮናታን ይህን ያድርግ፤ ይህንም ይጨምር፤ እግዚአብሔርም ከአባቴ ጋር እንደ ነበረ ከአንተ ጋር ይሁን።
ዮናታንም ዳዊትን፥ “በሰላም ሂድ፤ እነሆ፥ እኛ ሁለታችን በእኔና በአንተ፥ በዘሬና በዘርህ መካከል እግዚአብሔር ለዘለዓለም ምስክር ይሁን ብለን በእግዚአብሔር ስም ተማምለናል” አለው። ዳዊትም ተነሥቶ ሄደ፤ ዮናታንም ወደ ከተማ ገባ።
ዳዊትም፥ “ወደ እነዚያ ሠራዊት ልትመራኝ ትወድዳለህን?” አለው፥ እርሱም፥ “እንዳትገድለኝ፥ ለጌታዬም እጅ አሳልፈህ እንዳትሰጠኝ በአምላክ ማልልኝ፤ እኔም ወደ እነዚያ ሠራዊት እመራሃለሁ” አለው።