ዘፀአት 7:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴና አሮንም እንዲህ አደረጉ፤ እግዚአብሔር እንዳዘዛቸው አደረጉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴና አሮን እግዚአብሔር እንደ አዘዛቸው አደረጉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴና አሮንም እንዲሁ አደረጉ፤ ጌታ እንዳዘዛቸው አደረጉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴና አሮንም እግዚአብሔር ያዘዛቸውን ሁሉ ፈጸሙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴና አሮንም እንዲህ አደረጉ፤ እግዚአብሔር እንዳዘዛቸው አደረጉ። |
ሙሴም ሥራውን ሁሉ አየ፤ እነሆም፥ አድርገውት ነበር፤ እግዚአብሔር እንዳዘዘው እንዲሁ አድርገውት ነበር፤ ሙሴም ባረካቸው።
ሙሴና አሮንም ወደ ፈርዖን ገቡ፤ እግዚአብሔርም እንዳዘዛቸው እንዲሁ አደረጉ፤ አሮንም በትሩን በፈርዖንና በሹሞቹ ፊት ጣለ፤ እባብም ሆነች።
ያዘዝሁህን ነገር ሁሉ አንተ ትነግረዋለህ፤ ወንድምህም አሮን የእስራኤልን ልጆች ከሀገሩ ይለቅቅ ዘንድ ለፈርዖን ይንገረው።
ሙሴና አሮንም እግዚአብሔር እንዳዘዛቸው እንዲሁ አደረጉ፤ አሮንም በትሩን አነሣ፤ በፈርዖንና በሹሞቹ ፊት የወንዙን ውኃ መታ፤ የወንዙም ውኃ ሁሉ ተለውጦ ደም ሆነ።
የምትወዱኝ ብትሆኑ ትእዛዜን ጠብቁ፤ እኔ የአባቴን ትእዛዝ እንደ ጠበቅሁ፥ በፍቅሩም እንደምኖር እናንተም ትእዛዜን ብትጠብቁ በፍቅሬ ትኖራላችሁ።