ዘፀአት 5:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈርዖንም፥ “የእስራኤልን ልጆች እለቅቅ ዘንድ ቃሉን የምሰማው እርሱ እግዚአብሔር ማን ነው? እግዚአብሔርን አላውቅም፤ እስራኤልንም ደግሞ አልለቅቅም” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፈርዖንም “እንድታዘዘውና እስራኤልን እንድለቅለት ለመሆኑ ይህ እግዚአብሔር ማነው? እግዚአብሔርን አላውቅም፤ እስራኤልንም አልለቅም” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፈርዖንም፦ “ቃሉን እንድሰማ እስራኤልንስ እንድለቅ ጌታ ማን ነው? ጌታን አላውቅም፥ እስራኤልንም ደግሞ አልለቅቅም” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሡም “ለመሆኑ እግዚአብሔር ማን ነው? የእርሱንስ ትእዛዝ ሰምቼ እስራኤልን የምለቀው ለምንድን ነው? እኔ እግዚአብሔርን አላውቅም፤ እስራኤልንም አለቅም” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፈርዖንም፦ “ቃሉን እሰማ ዘንድ እስራኤልንስ እለቅቅ ዘንድ እግዚአብሔር ማን ነው? እግዚአብሔርን አላውቅም፤ እስራኤልንም ደግሞ አልለቅቅም፤” አለ። |
አምላካችሁስ ከእጄ እናንተን ለማዳን ይችል ዘንድ አባቶች ካጠፉአቸው ከአሕዛብ አማልክት ሁሉ ሕዝቡን ከእጄ ያድን ዘንድ የቻለ ማን ነው?
አሁንም ሕዝቅያስ አያስታችሁ፤ በእነዚህም ቃላት እንድትተማመኑ አያድርጋችሁ፤ አትመኑትም፤ ከአሕዛብና ከመንግሥታት አማልክት ሁሉ ሕዝቡን ከእጄና ከአባቶች እጅ ያድን ዘንድ ማንም አልቻለም፤ ስለዚህም አምላካችሁ ከእጄ ያድናችሁ ዘንድ አይችልም።”
እንደ ታበዩባቸውም ዐውቀህ ነበርና በፈርዖንና በባሪያዎቹ ሁሉ፥ በምድሩም ሕዝብ ሁሉ ላይ ምልክትንና ተአምራትን አሳየህ፤ ዛሬም እንደ ሆነው ስምህን አስጠራህ።
እግዚአብሔር በቤተ መቅደሱ ነው፤ እግዚአብሔር ዙፋኑ በሰማይ ነው፤ ዐይኖቹም ወደ ድሃ ይመለከታሉ፤ ቅንድቦቹም የሰው ልጆችን ይመረምራሉ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ በዚህ ታውቃለህ፤ እነሆ፥ እኔ የወንዙን ውኃ በእጄ ባለችው በትር እመታለሁ፤ ውኃውም ወደ ደም ይለወጣል።
“በእግዚአብሔር ላይ ኰርቶአልና፥ አስክሩት፤ ሞአብም በትፋቱ ላይ ይንከባለላል፤ በእጁም ያጨበጭባል፤ ደግሞ መሳቂያ ይሆናል።
እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱ መጠን እንዲሁ እግዚአብሔር ይህን የማይገባውን ይሠሩ ዘንድ ሰነፍ አእምሮን ሰጣቸው።
ትውልድ ሁሉ ደግሞ ወደ አባቶቻቸው ተጨመሩ፤ ከእነዚያም በኋላ እግዚአብሔርንና ለእስራኤልም ያደረገውን ሥራ ያላወቀ ሌላ ትውልድ ተነሣ።
ናባልም ተነሥቶ ለዳዊት ብላቴኖች መለሰላቸው እንዲህም አላቸው፥ “ዳዊት ማን ነው? የእሴይስ ልጅ ማን ነው? እያንዳንዳቸው ከጌቶቻቸው የኰበለሉ አገልጋዮች ዛሬ ብዙ ናቸው።