የወርቁንም መሠዊያ፥ የቅብዐቱንም ዘይት፥ ጣፋጩንም ዕጣን፥ የድንኳኑንም ደጃፍ መጋረጃ፤
የወርቅ መሠዊያው፣ ቅብዐ ዘይቱ፣ መልካም መዐዛ ያለው ዕጣን እንዲሁም የድንኳኑ መግቢያ መጋረጃ፤
የወርቁን መሠዊያ፥ የቅባቱን ዘይት፥ ጥሩ መዓዛ ያለው ዕጣን፥ የድንኳኑን ደጃፍ መጋረጃ፥
ከወርቅ የተሠራው መሠዊያ፥ የቅባቱ ዘይት፥ ጣፋጭ ሽታ ያለው ዕጣን፥ ለድንኳኑ ደጃፍ የተሠራለት መጋረጃ፥
የወርቁንም መሠዊያ፥ የቅብዓቱንም ዘይት፥ ጣፋጩንም ዕጣን፥ የድንኳኑንም ደጃፍ መጋረጃ፤
እነሆ፥ ለእስራኤል ለዘለዓለም እንደ ታዘዘው በእግዚአብሔር ፊት የጣፋጩን ሽቱ ዕጣን ለማጠን፥ የገጹንም ኅብስት ለማኖር፥ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት በጥዋትና በማታ፥ በሰንበታቱም፥ በመባቻዎቹም፥ በአምላካችንም በእግዚአብሔር በዓላት ለማቅረብ እኔ ልጁ ለአምላኬ ለእግዚአብሔር ስም ቤት እሠራለሁ፤ እርሱንም እቀድሳለሁ።
የመብራትም ዘይት፥ ለቅብዐት ዘይትና ለጣፋጭ ዕጣን ቅመም፥
“የዕጣን መሠዊያውን ከማይነቅዝ ዕንጨት ሥራ።
እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦
ወለሉንና የግድግዳውንም ዙሪያ፥ ቀንዶቹንም በጥሩ ወርቅ ትለብጠዋለህ፤ በዙሪያውም የጥሩ ወርቅ ክፈፍ ታደርግለታለህ።
አሮንም በጎ መዓዛ ያለው የደቀቀ ዕጣን በውስጡ በየማለዳው ይጠንበት፤ መብራቶቹን ሲያዘጋጅ ይጠነው።
የሚቀቡትን የቅብዐቱንም ዘይት፥ ለመቅደሱ የሚያጥኑትን ዕጣን እንዳዘዝሁህ ሁሉ ያድርጉ።”
ለመብራትም ዘይት፥ ለቅብዐት ሽቱን፥ ለማዕጠንት ዕጣንን፤
የተቀደሰውንም የቅብዐቱን ዘይት፥ ጥሩውንም የጣፋጭ ሽቱ ዕጣን በቀማሚ ብልሃት እንደ ተሠራ አደረገ።
ጥሩውንም መቅረዝ፥ መብራቶቹንም፥ በተራ የሚሆኑትንም ቀንዲሎች፥ ዕቃውንም ሁሉ፥ የመብራቱንም ዘይት፤
የናሱንም መሠዊያ፥ የናሱንም መከታ፥ መሎጊያዎቹንም፥ ዕቃውንም ሁሉ፥ የመታጠቢያውን ሰንም፥ መቀመጫውንም፤