La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፀአት 30:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ለነ​ፍ​ሳ​ችሁ ቤዛ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስጦታ ስት​ሰጡ ባለ ጠጋው ከሰ​ቅል ግማሽ አይ​ጨ​ምር፤ ድሃ​ውም አያ​ጕ​ድል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ለሕይወታችሁ ማስተስረያ እንዲሆን ለእግዚአብሔር መሥዋዕት በምታቀርቡበት ጊዜ ባለጠጋው ከግማሽ ሰቅል በላይ፣ ድኻውም አጕድሎ አይስጥ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ለነፍሳችሁ ማስተስረያ የጌታን ስጦታ ስትሰጡ፥ ከግማሽ ሰቅሉ ባለ ጠጋው አይጨምር፥ ደሃውም አያጉድል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ለሕይወታቸው ቤዛ ይህን መባ ሲያቀርቡ ሀብታሙም ሆነ ድኻው እኩል ይክፈል እንጂ የሀብታሙ ክፍያ ብዙ የድኻው ክፍያ አነስተኛ አይሁን።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ለነፍሳችሁ ማስተስረያ የእግዚአብሔርን ስጦታ ስትሰጡ ባለ ጠጋው ከሰቅል ግማሽ አይጨምር፥ ደሀውም አያጉድል።

Ver Capítulo



ዘፀአት 30:15
12 Referencias Cruzadas  

ዳዊ​ትም የገ​ባ​ዖ​ንን ሰዎች፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ርስት ትባ​ርኩ ዘንድ ምን ላድ​ር​ግ​ላ​ችሁ? ማስ​ተ​ስ​ረ​ያ​ውስ ምን​ድን ነው?” አላ​ቸው።


እርሱ ግን የክ​ቡ​ርን ሰው ፊት አያ​ፍ​ርም። ለታ​ላ​ቁም ክብር መስ​ጠ​ትን አያ​ው​ቅም፥ ከፊ​ታ​ቸ​ውም አይ​ሸ​ሽም።


“አንተ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ቍጥር የወ​ሰ​ድህ እንደ ሆነ በቈ​ጠ​ር​ሃ​ቸው ጊዜ መቅ​ሠ​ፍት እን​ዳ​ይ​ሆ​ን​ባ​ቸው፥ በቈ​ጠ​ር​ሃ​ቸው ጊዜ ከእ​ነ​ርሱ ሰው ሁሉ እንደ ቍጥ​ራ​ቸው መጠን የነ​ፍ​ሱን ቤዛ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይስጥ።


ይቈ​ጠር ዘንድ የሚ​ያ​ል​ፈው ሁሉ፥ ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም ከፍ ያለ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስጦታ ይሰ​ጣል።


የማ​ስ​ተ​ስ​ረ​ያ​ው​ንም ገን​ዘብ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ወስ​ደህ ለም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ማገ​ል​ገያ ትሰ​ጠ​ዋ​ለህ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ለነ​ፍ​ሳ​ችሁ ቤዛ እን​ዲ​ሆን ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መታ​ሰ​ቢያ ይሁን።”


እያ​ን​ዳ​ን​ዱም ሰው አንድ አንድ ዲድ​ር​ክም አዋጣ፤ አንድ ዲድ​ር​ክም እንደ መቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን የሰ​ቅል ግማሽ ነው፤ ይህም የተ​ዋ​ጣው ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ከተ​ቈ​ጠሩ ሁሉ ስድ​ስት መቶ ሦስት ሺህ አም​ስት መቶ አምሳ ሰዎች ነበረ።


ባለ ጠጋና ድሃ በአንድነት ተገናኙ፤ ሁለቱንም እግዚአብሔር ፈጠራቸው።


የሀ​ገ​ሩም ሕዝብ ሁሉ ይህን መባ ለእ​ስ​ራ​ኤል አለቃ ይሰ​ጣሉ።


የሥጋ ሁሉ ሕይ​ወት ደሙ ነው፤ ደሙም ከሕ​ይ​ወቱ የተ​ነሣ ያስ​ተ​ሰ​ር​ያ​ልና በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ለነ​ፍ​ሳ​ችሁ ማስ​ተ​ስ​ረያ ይሆን ዘንድ እኔ ለእ​ና​ንተ ሰጠ​ሁት።


ሰውም ሁሉ ከአ​ገ​ኘው ከወ​ርቅ ዕቃ፥ ከእ​ግር አል​ቦም፥ ከአ​ም​ባ​ርም፥ ከቀ​ለ​በ​ትም ከጕ​ት​ቻም፥ ከድ​ሪ​ውም ስለ እኛ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ታስ​ተ​ሰ​ር​ዩ​ልን ዘንድ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መባ አም​ጥ​ተ​ናል” አሉት።


እና​ን​ተም ጌቶች ሆይ፥ ቍጣ​ች​ሁን እያ​በ​ረ​ዳ​ችሁ፥ በደ​ላ​ቸ​ው​ንም ይቅር እያ​ላ​ችሁ፥ ትክ​ክ​ለ​ኛ​ውን አድ​ር​ጉ​ላ​ቸው፤ ፊት አይቶ የማ​ያ​ዳላ ጌታ በእ​ነ​ር​ሱና በእ​ና​ንተ ላይ በሰ​ማይ እንደ አለ ታው​ቃ​ላ​ች​ሁና።


የሚ​በ​ድል ግን ፍዳ​ውን ያገ​ኛል፤ እር​ሱም አያ​ደ​ላ​ለ​ትም።