ዘፀአት 12:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ይህ ወር የወሮች መጀመሪያ ይሁናችሁ፤ የዓመቱም መጀመሪያ ወር ይሁናችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ይህ ወር ለእናንተ የወር መጀመሪያ፣ የዓመቱም መጀመሪያ ይሁንላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ይህ ወር የወሮች መጀመሪያ ይሁናችሁ፤ ከዓመቱ ወሮችም የመጀመሪያ ይሁናችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ይህ ወር ለእናንተ የዓመቱ መጀመሪያ ወር ይሁንላችሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) “ይህ ወር የወሮች መጀመሪያ ይሁናችሁ፤ የዓመቱም መጀመሪያ ወር ይሁናችሁ። |
ከመጀመሪያውም ወር በዐሥራ አራተኛው ቀን ሠርክ ጀምራችሁ እስከዚሁ ወር ሃያ አንደኛ ቀን ሠርክ ድረስ ቂጣ ትበላላችሁ።
ለእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ ተናገሩ፤ በሉአቸውም፦ በዚህ ወር በዐሥረኛው ቀን ሰው ሁሉ ለአባቱ ቤተ ሰቦች ቤቶች አንድ አንድ ጠቦት፥ እያንዳንዱ ሰውም ለራሱ ቤተ ሰብእ አንድ ጠቦት ይውሰድ።
ሙሴም ሕዝቡን አለ፥ “ከባርነት ቤት ከግብፅ የወጣችሁባትን ይህችን ቀን ዐስቡ፤ እግዚአብሔር ከዚህ ቦታ በበረታች እጅ አውጥቶአችኋልና። ስለዚህ የቦካ እንጀራ አትብሉ።
የቂጣውን በዓል ጠብቁ፤ በአዲስ ወር ከግብፅ ምድር ወጥታችኋልና በዚህ ወር እንዳዘዝኋችሁ ሰባት ቀን ቂጣ ትበላላችሁ።
“የቂጣውን በዓል ትጠብቀዋለህ። በሚያዝያ ወር ከግብፅ ወጥተሃልና በታዘዘው ዘመን በሚያዝያ ወር እንዳዘዝሁህ ሰባት ቀን ቂጣ ብላ።
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “በመጀመሪያው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ከመንጋው ነውር የሌለበትን ወይፈን ውሰድ፤ መቅደሱንም አንጻ።
“በመጀመሪያው ወር ከወሩም በዐሥራ አራተኛው ቀን የፋሲካን በዓል ታደርጋላችሁ። እስከ ሰባት ቀንም ድረስ ቂጣ ትበላላችሁ።
“በሚያዝያ ወር ከግብፅ ሀገር በሌሊት ወጥተሃልና የሚያዝያን ወር ጠብቀህ፥ የአምላክህ የእግዚአብሔርን ፋሲካ አድርግ።