“እጅህን በእጄ ላይ አድርግ፤ እኔም አብሬ ከምኖራቸው ከከነዓን ሴቶች ልጆች ለልጄ ለይስሐቅ ሚስት እንዳትወስድለት በሰማይና በምድር አምላክ በእግዚአብሔር አምልሃለሁ፤
ዘዳግም 6:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላክህን እግዚአብሔርን ፍራ፤ እርሱንም ብቻ አምልክ፤ እርሱንም ተከተል በስሙም ማል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላክህን እግዚአብሔርን ፍራ፤ እርሱን ብቻ አገልግል፤ በስሙም ማል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ እግዚአብሔርን ፍራ፤ እርሱንም አምልክ፥ በስሙም ማል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላክህን እግዚአብሔርን በመፍራት አክብረው፤ እርሱን ብቻ አምልክ፤ መሐላህም በእርሱ ስም ብቻ ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምላክህን እግዚአብሔርን ፍራ፤ እርሱንም አምልክ፤ በስሙም ማል። |
“እጅህን በእጄ ላይ አድርግ፤ እኔም አብሬ ከምኖራቸው ከከነዓን ሴቶች ልጆች ለልጄ ለይስሐቅ ሚስት እንዳትወስድለት በሰማይና በምድር አምላክ በእግዚአብሔር አምልሃለሁ፤
ነገር ግን በታላቅ ኀይል በተዘረጋችም ክንድ ከግብፅ ምድር ያወጣችሁን እግዚአብሔርን እርሱን ፍሩ፤ ለእርሱም ስገዱ፤ ለእርሱም ሠዉ።
“የእግዚአብሔርን የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ፤ አምላክህ እግዚአብሔር ስሙን በከንቱ የሚጠራውን ከበደል አያነጻውምና።
አምላክህንም እግዚአብሔርን ታመልካለህ፤ እኔ እህልህንና ወይንህን፥ ውኃህንም እባርካለሁ፤ በሽታንም ከአንተ አርቃለሁ።
ቃሌ ከአፌ በጽድቅ ወጥታለች፤ አትመለስምም፤ ጕልበት ሁሉ ለእኔ ይንበረከካል፤ ምላስም ሁሉ በእግዚአብሔር ይምላል ብዬ በራሴ ምያለሁ።”
እናንተ በእስራኤል ስም የተጠራችሁ፥ ከይሁዳም የወጣችሁ፥ በእውነት ሳይሆን፥ በጽድቅም ሳይሆን እርሱን እየጠራችሁ በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ስም የምትምሉ የያዕቆብ ቤት ሆይ፥ ይህን ስሙ፤
እንዲሁም በምድር ላይ የተባረኩ ይሆናሉ፤ እውነተኛውን አምላክ ያመሰግናሉና፥ በምድርም ላይ በእውነተኛው አምላክ ይምላሉና፤ የቀድሞውንም ጭንቀት ረስተዋልና፤ በልቡናቸውም አያስቡትምና።
በበዓል ይምሉ ዘንድ ሕዝቤን እንዳስተማሩ በስሜ፦ ሕያው እግዚአብሔርን! ብለው ይምሉ ዘንድ የሕዝቤን መንገድ ፈጽመው ቢማሩ፥ በዚያ ጊዜ በሕዝቤ መካከል ይመሠረታሉ።
ሕያው እግዚአብሔርን! ብሎ በእውነትና በቅንነት፤ በጽድቅም ቢምል፥ አሕዛብ በእርሱ ይባረካሉ፤ በኢየሩሳሌምም እግዚአብሔርን ያመሰግናሉ።
“ከእነዚህ ነገሮች በየትኛው ይቅር እልሻለሁ? ልጆችሽ ትተውኛል፤ አማልክትም ባልሆኑ ምለዋል፤ አጠገብኋቸውም፤ እነርሱ ግን አመነዘሩ፤ በአመንዝራዎቹም ቤት ዐደሩ።
ጌታችን ኢየሱስም መልሶ፥ “ሰይጣን ከኋላዬ ሂድ ለእግዚአብሔር ለአምላክህ ልትሰግድ፥ እርሱንም ብቻ ልታመልክ ተጽፎአል” አለው።
“እስራኤል ሆይ፥ አሁንስ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ የሚፈልገው ምንድን ነው? አምላክህን እግዚአብሔርን ትፈራ ዘንድ፥ በመንገዱም ሁሉ ትሄድ ዘንድ፥ አምላክህንም እግዚአብሔርን ትወድድ ዘንድ፥ በፍጹምም ልብህ፥ በፍጹምም ነፍስህ ታመልከው ዘንድ ነው እንጂ፥
ከግብፅ ምድር ካወጣችሁ፥ ከባርነትም ቤት ካዳናችሁ ከአምላካችሁ ከእግዚአብሔር ሊያስታችሁ፥ አምላክህ እግዚአብሔርም ትሄድባት ዘንድ ካዘዘህ መንገድ ሊያወጣህ ተናግሮአልና ያ ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ይገደል፤ እንዲሁም ክፉውን ነገር ከአንተ አርቅ።
“የእግዚአብሔርን የአምላክህን ስም በሐሰት አትጥራ፤ እግዚአብሔር ስሙን በሐሰት የሚጠራውን ከበደል አያነጻውምና።
ለእነርሱ፥ ለዘለዓለምም ለልጆቻቸው መልካም ይሆንላቸው ዘንድ፥ እንዲፈሩኝ፥ ሁልጊዜም ትእዛዜን ሁሉ እንዲጠብቁ እንዲህ ያለ ልብ ማን በሰጣቸው፥
እናንተ፥ ልጆቻችሁም፥ የልጅ ልጆቻችሁም በዕድሜአችሁ ሁሉ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ፈርታችሁ እኔ ለእናንተ ያዘዝሁትን ሥርዐቱንና ትእዛዙን ሁሉ ትጠብቁ ዘንድ፥ ዕድሜአችሁም ይረዝም ዘንድ፤
አሁንም፥ በእግዚአብሔር ማሉልኝ፤ እኔ ለእናንተ ቸርነት እንደ አደረግሁ እናንተ ደግሞ ለአባቴ ቤት ቸርነት እንድታደርጉ፥ በእውነት ምልክት ስጡኝ።
በእናንተም መካከል ወደ ቀሩት ወደ እነዚህ አሕዛብ አትግቡ፤ የአማልክቶቻቸውም ስሞች በእናንተ መካከል አይጠሩ፤ አትማሉባቸውም፤ አታምልኳቸውም፤ አትስገዱላቸውም፤
“አሁንም እግዚአብሔርን ፍሩት፤ በእውነትና በቅንነትም አምልኩት፤ አባቶቻችሁም በወንዝ ማዶ፥ በግብፅም ውስጥ ያመለኩአቸውን ሌሎች አማልክት ከእናንተ አርቁ፤ እግዚአብሔርንም አምልኩ።
ዳዊትም፥ “እኔ በፊትህ ሞገስን እንዳገኘሁ አባትህ በእውነት ያውቃል፤ እርሱም፦ ዮናታን እንዳይቃወም አይወቅ ይላል፤ ነገር ግን ሕያው እግዚአብሔርን! በሕያው ነፍስህም እምላለሁ፤ እኔ እንዳልሁት በእኔና በሞት መካከል አንድ ርምጃ ያህል ቀርቶአል” ብሎ ማለ።
ሳሙኤልም የእስራኤልን ቤት ሁሉ፥ “በሙሉ ልባችሁ ወደ እግዚአብሔር ከተመለሳችሁ እንግዶችን አማልክትና ምስሎቻቸውን ከመካከላችሁ አርቁ፤ ልባችሁንም ወደ እግዚአብሔር አቅኑ፤ እርሱንም ብቻ አምልኩ፤ እርሱም ከፍልስጥኤማውያን እጅ ያድናችኋል” ብሎ ተናገራቸው።