እኛም ከሊባኖስ የምትሻውን ያህል እንጨት እንቈርጣለን፤ በታንኳም አድርገን በባሕር ላይ ወደ አንተ ወደ ኢዮጴ እንልካለን፤ አንተም ወደ ኢየሩሳሌም ታስወስደዋለህ።”
ሐዋርያት ሥራ 9:42 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በኢዮጴም ያሉ ሁሉ ይህን ሰሙ፤ ብዙዎችም በጌታችን አመኑ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህም ነገር በመላው ኢዮጴ ታወቀ፤ ብዙ ሰዎችም በጌታ አመኑ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህም በኢዮጴ ሁሉ የታወቀ ሆነ፤ ብዙ ሰዎችም በጌታ አመኑ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም ነገር በኢዮጴ ሁሉ ታወቀ፤ ብዙ ሰዎችም በጌታ አመኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህም በኢዮጴ ሁሉ የታወቀ ሆነ፥ ብዙ ሰዎችም በጌታ አመኑ። |
እኛም ከሊባኖስ የምትሻውን ያህል እንጨት እንቈርጣለን፤ በታንኳም አድርገን በባሕር ላይ ወደ አንተ ወደ ኢዮጴ እንልካለን፤ አንተም ወደ ኢየሩሳሌም ታስወስደዋለህ።”
ዮናስ ግን ከእግዚአብሔር ፊት ወደ ተርሴስ ይሸሽ ዘንድ ተነሣ፤ ወደ ኢዮጴም ወረደ፤ ወደ ተርሴስም የምታልፍ መርከብ አገኘ፤ ከእግዚአብሔርም ፊት ኰብልሎ ከእነርሱ ጋር ወደ ተርሴስ ይሄድ ዘንድ ዋጋ ሰጥቶ ወደ እርስዋ ገባ።
ጌታችን ኢየሱስም ሰምቶ እንዲህ አለ፥ “ይህ ደዌ በእርሱ የእግዚአብሔር ልጅ ይከብር ዘንድ ስለ እግዚአብሔር ክብር ነው እንጂ ለሞት አይደለም።”
ስለዚህ ከአይሁድም ወደ ማርታና ወደ ማርያም መጥተው የነበሩ ብዙ ሰዎች ጌታችን ኢየሱስ ያደረገውን አይተው በእርሱ አመኑ።
ጌታችን ኢየሱስም ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ አለ፥ “በእኔ የሚያምን በላከኝም ነው እንጂ በእኔ ብቻ የሚያምን አይደለም።
እርሱም በቤቱ ቆሞ ሳለ የእግዚአብሔርን መልአክ እንዳየ ‘ወደ ኢዮጴ ከተማ ልከህ ጴጥሮስ የተባለውን ስምዖንን ይጥሩልህ።
“በኢዮጴ ከተማ ሳለሁ ስጸልይ ተመስጦ መጣብኝና ራእይ አየሁ፤ ታላቅ መጋረጃ የመሰለ ዕቃ በአራቱ ማዕዘን ተይዞ ከሰማይ ወረደ፤ ወደ እኔም መጣ።
በኢዮጴ ሀገርም ጣቢታ የምትባል አንዲት ደቀ መዝሙር ነበረች፤ በትርጓሜውም ዶርቃስ ይሉአታል፤ ፌቆ ማለት ነው፤ እርስዋም ብዙ ደጋግ ሥራ ትሠራ ነበር፤ ምጽዋትም ትሰጥ ነበር።
ልዳም ለኢዮጴ ቅርብ ነበርና ደቀ መዛሙርት ጴጥሮስ በዚያ እንዳለ ሰምተው ወደ እነርሱ መምጣት እንዳይዘገይ ይማልዱት ዘንድ ሁለት ሰዎችን ወደ እርሱ ላኩ።