Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 9:38 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

38 ልዳም ለኢ​ዮጴ ቅርብ ነበ​ርና ደቀ መዛ​ሙ​ርት ጴጥ​ሮስ በዚያ እን​ዳለ ሰም​ተው ወደ እነ​ርሱ መም​ጣት እን​ዳ​ይ​ዘ​ገይ ይማ​ል​ዱት ዘንድ ሁለት ሰዎ​ችን ወደ እርሱ ላኩ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

38 ልዳ ለኢዮጴ ቅርብ ስለ ነበረች፣ ደቀ መዛሙርትም ጴጥሮስ በልዳ መሆኑን በሰሙ ጊዜ ሁለት ሰዎች ልከው፣ “እባክህ ፈጥነህ ወደ እኛ ና!” ሲሉ ለመኑት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

38 ልዳም ለኢዮጴ ቅርብ ናትና ደቀ መዛሙርት ጴጥሮስ በዚያ እንዳለ ሰምተው፥ ወደ እነርሱ ከመምጣት እንዳይዘገይ እየለመኑ ሁለት ሰዎች ወደ እርሱ ላኩ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

38 ልዳ ለኢዮጴ ቅርብ ስለ ነበረች በኢዮጴ ያሉት ደቀ መዛሙርት ጴጥሮስ በልዳ መኖሩን ሰምተው “እባክህን ሳትዘገይ በቶሎ ድረስልን” ብለው ሁለት ሰዎች ላኩበት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

38 ልዳም ለኢዮጴ ቅርብ ናትና ደቀ መዛሙርት ጴጥሮስ በዚያ እንዳለ ሰምተው፥ ወደ እነርሱ ከመምጣት እንዳይዘገይ እየለመኑ ሁለት ሰዎች ወደ እርሱ ላኩ።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 9:38
15 Referencias Cruzadas  

በኢ​ዮጴ ሀገ​ርም ጣቢታ የም​ት​ባል አን​ዲት ደቀ መዝ​ሙር ነበ​ረች፤ በት​ር​ጓ​ሜ​ውም ዶር​ቃስ ይሉ​አ​ታል፤ ፌቆ ማለት ነው፤ እር​ስ​ዋም ብዙ ደጋግ ሥራ ትሠራ ነበር፤ ምጽ​ዋ​ትም ትሰጥ ነበር።


በቤተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ንም አንድ ዓመት አብ​ረው ተቀ​መጡ፤ ብዙ ሕዝ​ብ​ንም አስ​ተ​ማሩ፤ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ትም መጀ​መ​ሪያ በአ​ን​ጾ​ኪያ ክር​ስ​ቲ​ያን ተብ​ለው ተጠሩ።


ከዚ​ህም በኋላ ጴጥ​ሮስ በየ​ቦ​ታዉ ሲዘ​ዋ​ወር በልዳ ወደ​ሚ​ኖ​ሩት ቅዱ​ሳን ዘንድ ደረሰ።


በባ​ሕር በኩል በኢ​ዮጴ ፊት ለፊት ካለው ዳርቻ ጋር ኢያ​ራ​ቆን።


እኛም ከሊ​ባ​ኖስ የም​ት​ሻ​ውን ያህል እን​ጨት እን​ቈ​ር​ጣ​ለን፤ በታ​ን​ኳም አድ​ር​ገን በባ​ሕር ላይ ወደ አንተ ወደ ኢዮጴ እን​ል​ካ​ለን፤ አን​ተም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ታስ​ወ​ስ​ደ​ዋ​ለህ።”


ለጠ​ራ​ቢ​ዎ​ችና ለአ​ና​ጢ​ዎ​ችም ብር ሰጡ፤ የፋ​ር​ስም ንጉሥ ቂሮስ እንደ ፈቀ​ደ​ላ​ቸው የዝ​ግባ ዛፍ ከሊ​ባ​ኖስ በባ​ሕር ወደ ኢዮጴ ያመጡ ዘንድ ለሲ​ዶ​ናና ለጢ​ሮስ ሰዎች መብ​ልና መጠጥ፥ ዘይ​ትም ሰጡ።


ዮናስ ግን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ወደ ተር​ሴስ ይሸሽ ዘንድ ተነሣ፤ ወደ ኢዮ​ጴም ወረደ፤ ወደ ተር​ሴ​ስም የም​ታ​ልፍ መር​ከብ አገኘ፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ኰብ​ልሎ ከእ​ነ​ርሱ ጋር ወደ ተር​ሴስ ይሄድ ዘንድ ዋጋ ሰጥቶ ወደ እር​ስዋ ገባ።


እህ​ልም በላ፤ በረ​ታም፤ ጥቂት ቀንም ከደቀ መዛ​ሙ​ርት ጋር በደ​ማ​ስቆ ሰነ​በተ።


በኢ​ዮ​ጴም ያሉ ሁሉ ይህን ሰሙ፤ ብዙ​ዎ​ችም በጌ​ታ​ችን አመኑ።


ጴጥ​ሮ​ስም በኢ​ዮጴ በቍ​ር​በት ፋቂው በስ​ም​ዖን ቤት ብዙ ቀን ተቀ​መጠ።


አሁ​ንም ጴጥ​ሮስ የሚ​ባ​ለ​ውን ስም​ዖ​ንን ይጠ​ሩ​ልህ ዘንድ ወደ ኢዮጴ ከተማ ሰዎ​ችን ላክ።


ነገ​ሩ​ንም ሁሉ ነግሮ ወደ ኢዮጴ ከተማ ላካ​ቸው።


“በኢ​ዮጴ ከተማ ሳለሁ ስጸ​ልይ ተመ​ስጦ መጣ​ብ​ኝና ራእይ አየሁ፤ ታላቅ መጋ​ረጃ የመ​ሰለ ዕቃ በአ​ራቱ ማዕ​ዘን ተይዞ ከሰ​ማይ ወረደ፤ ወደ እኔም መጣ።


እር​ሱም በቤቱ ቆሞ ሳለ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መል​አክ እን​ዳየ ‘ወደ ኢዮጴ ከተማ ልከህ ጴጥ​ሮስ የተ​ባ​ለ​ውን ስም​ዖ​ንን ይጥ​ሩ​ልህ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios