ሐዋርያት ሥራ 11:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በኢዮጴ ከተማ ሳለሁ ስጸልይ ተመስጦ መጣብኝና ራእይ አየሁ፤ ታላቅ መጋረጃ የመሰለ ዕቃ በአራቱ ማዕዘን ተይዞ ከሰማይ ወረደ፤ ወደ እኔም መጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በኢዮጴ ከተማ ስጸልይ በተመስጦ ውስጥ እያለሁ ራእይ አየሁ፤ ትልቅ ጨርቅ የሚመስል ነገር፣ በአራት ማእዘን ተይዞ ከሰማይ እኔ ወደ ነበርሁበት ቦታ ሲወርድ አየሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እኔ በኢዮጴ ከተማ ስጸልይ ሳለሁ ተመስጬ ራእይን አየሁ፤ ታላቅ ሸማ የመሰለ ዕቃ በአራት ማዕዘን ተይዞ ከሰማይ ወረደና ወደ እኔ መጣ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እኔ በኢዮጴ ከተማ በጸሎት ላይ ሳለሁ በተመስጦ ራእይ አየሁ፤ ያየሁትም ትልቅ የመጋረጃ ጨርቅ የሚመስል ነገር በአራት ማእዘን ተይዞ ከሰማይ ሲወርድና ወደ እኔ ሲመጣ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) “እኔ በኢዮጴ ከተማ ስጸልይ ሳለሁ ተመስጬ ራእይን አየሁ፤ ታላቅ ሸማ የመሰለ ዕቃ በአራት ማዕዘን ተይዞ ከሰማይ ወረደና ወደ እኔ መጣ፤ |
እርሱም፥ “አሞጽ ሆይ! የምታየው ምንድን ነው?” አለኝ። እኔም፥ “የቃርሚያ ፍሬ የሞላበት ዕንቅብ ነው” አልሁት። እግዚአብሔርም አለኝ፥ “ፍጻሜ በሕዝቤ በእስራኤል ላይ መጥቶአል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ደግሞ ይቅር አልላቸውም።
በደማስቆም ስሙን ሐናንያ የሚሉት አንድ ደቀ መዝሙር ነበር፤ ጌታም በራእይ ተገልጦ፥ “ሐናንያ” ብሎ ጠራው፤ እርሱም፥ “አቤቱ፥ እነሆኝ” አለ።
በኢዮጴ ሀገርም ጣቢታ የምትባል አንዲት ደቀ መዝሙር ነበረች፤ በትርጓሜውም ዶርቃስ ይሉአታል፤ ፌቆ ማለት ነው፤ እርስዋም ብዙ ደጋግ ሥራ ትሠራ ነበር፤ ምጽዋትም ትሰጥ ነበር።
ልዳም ለኢዮጴ ቅርብ ነበርና ደቀ መዛሙርት ጴጥሮስ በዚያ እንዳለ ሰምተው ወደ እነርሱ መምጣት እንዳይዘገይ ይማልዱት ዘንድ ሁለት ሰዎችን ወደ እርሱ ላኩ።