ዔሳውም አባቱ ስለ ባረከው በያዕቆብ ቂም ያዘበት፤ ዔሳውም በልቡ አለ፥ “ለአባቴ የልቅሶ ቀን ትቅረብ፤ ወንድሜን ያዕቆብን እገድለዋለሁ።”
2 ሳሙኤል 11:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኦርዮም ሚስት ባልዋ ኦርዮ እንደ ሞተ በሰማች ጊዜ ለባልዋ አለቀሰች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የኦርዮን ሚስት ባሏ መሞቱን በሰማች ጊዜ ዐዘነች፤ አለቀሰችለትም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የኦርዮ ሚስት ባሏ መሞቱን በሰማች ጊዜ ኀዘን ተቀመጠች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የኦርዮ ሚስት ባልዋ እንደ ተገደለ በሰማች ጊዜ በማልቀስ አዘነችለት፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የኦርዮም ሚስት ባልዋ ኦርዮ እንደሞተ በሰማች ጊዜ ለባልዋ አለቀሰች። |
ዔሳውም አባቱ ስለ ባረከው በያዕቆብ ቂም ያዘበት፤ ዔሳውም በልቡ አለ፥ “ለአባቴ የልቅሶ ቀን ትቅረብ፤ ወንድሜን ያዕቆብን እገድለዋለሁ።”
በዮርዳኖስ ማዶ ወዳለችው ወደ አጣድ አውድማ ደረሱ፤ እጅግ ታላቅ በሆነ በጽኑ ልቅሶም አለቀሱለት፤ ለአባቱም ሰባት ቀን ልቅሶ አደረገለት።
ዳዊትም መልእክተኛውን፥ “ሰይፍ አንድ ጊዜ ይህን፥ አንድ ጊዜም ያን ይበላልና ይህ ነገር በዐይንህ አይክፋ፤ ከተማዪቱን የሚወጉትን አበርታ፤ አፍርሳትም ብለህ ለኢዮአብ ንገረው፤ አንተም አጽናው” አለው።
ኢዮአብም ወደ ቴቁሔ ልኮ ከዚያ ብልሃተኛ ሴት አስመጣና፥ “አልቅሺ፤ የኀዘንም ልብስ ልበሺ፤ ዘይትም አትቀቢ፤ ስለ ሞተ ሰውም ብዙ ዘመን እንደምታለቅስ ሴት ሁኚ፤
ዳዊትም ኢዮአብንና ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሕዝብ ሁሉ፥ “ልብሳችሁን ቅደዱ፤ ማቅም ልበሱ፤ በአበኔርም ፊት አልቅሱ” አላቸው። ንጉሡም ዳዊት ከቃሬዛው በኋላ ሄደ።
ቀትርም በሆነ ጊዜ ወጡ፤ ወልደ አዴርም በማቅ ድንኳን ውስጥ ጠጥቶ ሰክሮ ነበረ፤ የሚረዱት ሠላሳ ሁለት ነገሥታትም አብረውት ነበሩ።
የእስራኤልም ልጆች በዮርዳኖስ በኢያሪኮ አቅራቢያ በሞዓብ ሜዳ ሠላሳ ቀን ለሙሴ አለቀሱለት፤ ለሙሴም ያለቀሱለት የልቅሶው ወራት ተፈጸመ።