La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ነገሥት 13:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ በጣም ተቈጣ፤ በዘ​መ​ኑም ሁሉ በሶ​ር​ያው ንጉሥ በአ​ዛ​ሄል እጅ፥ በአ​ዛ​ሄ​ልም ልጅ በወ​ልደ አዴር እጅ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የእግዚአብሔር ቍጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፤ ስለዚህ የሶርያ ንጉሥ አዛሄልና ልጁ ቤን ሃዳድ በነበሩበት ዘመን ሁሉ አሳልፎ በእጃቸው ሰጣቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ስለዚህም እግዚአብሔር በእስራኤል ሕዝብ ላይ ተቆጥቶ ለሶርያ ንጉሥ አዛሄል፥ እንዲሁም ለልጁ ለቤንሀዳድ በተደጋጋሚ አሳልፎ ሰጥቶአቸዋል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስለዚህም እግዚአብሔር በእስራኤል ሕዝብ ላይ ተቈጥቶ ለሶርያ ንጉሥ አዛሄል፥ እንዲሁም ለልጁ ለቤንሀዳድ በተደጋጋሚ አሳልፎ ሰጥቶአቸዋል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የእግዚአብሔርም ቍጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፤ በዘመኑም ሁሉ በሶርያው ንጉሥ በአዛሄል እጅ፥ በአዛሄልም ልጅ በቤንሀዳድ እጅ አሳልፎ ይሰጣቸው ነበር።

Ver Capítulo



2 ነገሥት 13:3
16 Referencias Cruzadas  

ከአ​ዛ​ሄ​ልም ሰይፍ የሚ​ያ​መ​ል​ጠ​ውን ሁሉ ኢዩ ይገ​ድ​ለ​ዋል፤ ከኢ​ዩም ሰይፍ የሚ​ያ​መ​ል​ጠ​ውን ሁሉ ኤል​ሳዕ ይገ​ድ​ለ​ዋል።


በዚ​ያም ወራት የሶ​ርያ ንጉሥ አዛ​ሄል ዘመተ፤ ጌት​ንም ወግቶ ያዛት፤ አዛ​ሄ​ልም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ለመ​ው​ጣት ፊቱን አቀና።


አዛ​ሄ​ልም በኢ​ዮ​አ​ካዝ ዘመን ሁሉ እስ​ራ​ኤ​ልን አስ​ጨ​ነቀ፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል ዘር ሁሉ ተቈጣ፤ አስ​ጨ​ነ​ቃ​ቸ​ውም፤ ከፊ​ቱም እስ​ኪ​ጥ​ላ​ቸው ድረስ በበ​ዝ​ባ​ዦች እጅ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው።


በደ​ማ​ስ​ቆም ቅጥር ላይ እሳት አነ​ድ​ዳ​ለሁ፤ የወ​ልደ አዴ​ር​ንም አዳ​ራ​ሾች ትበ​ላ​ለች።”


ፊቴ​ንም አከ​ብ​ድ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ፊት ትወ​ድ​ቃ​ላ​ችሁ፤ የሚ​ጠ​ሏ​ች​ሁም ያሸ​ን​ፉ​አ​ች​ኋል። ማንም ሳያ​ሳ​ድ​ዳ​ችሁ ትሸ​ሻ​ላ​ችሁ።


“በግ​ብፅ እንደ ሆነው ሞትን ሰደ​ድ​ሁ​ባ​ችሁ፤ ጐበ​ዛ​ዝ​ቶ​ቻ​ች​ሁን በሰ​ይፍ ገደ​ልሁ፤ ፈረ​ሶ​ቻ​ች​ሁ​ንም አስ​ማ​ረ​ክሁ፤ በሰ​ፈ​ራ​ች​ሁም እሳ​ትን ሰድጄ አጠ​ፋ​ኋ​ችሁ፤ በዚ​ህም ሁሉ እና​ንተ ወደ እኔ አል​ተ​መ​ለ​ሳ​ች​ሁም፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከጠ​ላ​ቶ​ችህ ፊት የተ​መ​ታህ ያደ​ር​ግ​ሃል፤ በአ​ንድ መን​ገድ ትወ​ጣ​ባ​ቸ​ዋ​ለህ፤ በሰ​ባት መን​ገ​ድም ከእ​ነ​ርሱ ትሸ​ሻ​ለህ፤ በም​ድ​ርም መን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ የተ​በ​ተ​ንህ ትሆ​ና​ለህ።


አም​ላ​ካ​ችን በእ​ው​ነት የሚ​ያ​ቃ​ጥል እሳት ነውና።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ተቈጣ፤ ወደ ማረ​ኳ​ቸ​ውም ማራ​ኪ​ዎች እጅ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው፤ ማረ​ኩ​አ​ቸ​ውም፤ በዙ​ሪ​ያ​ቸ​ውም ባሉት በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው እጅ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው፤ ከዚ​ያም ወዲያ ጠላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ሊቋ​ቋሙ አል​ቻ​ሉም።


ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ፈጽሞ ተቈጣ፤ በወ​ን​ዞ​ችም መካ​ከል ባለች በሶ​ርያ ንጉሥ በኩ​ሳ​ር​ሳ​ቴም እጅ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ለኩ​ሳ​ር​ሳ​ቴም ስም​ንት ዓመት ተገ​ዙ​ለት።