ነገር ግን በጎ ነገር በተደረገልህ ጊዜ እኔን ዐስበኝ፤ ምሕረትንም አድርግልኝ፤ ስለ እኔም ለፈርዖን አሳስበህ ከዚህ እስር ቤት አውጣኝ፤
1 ሳሙኤል 25:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህ ርኵሰትና የልብ በደል፥ በከንቱ ንጹሕ ደም ማፍሰስም ለጌታዬ አይሁኑበት፤ የጌታዬም እጁ ትዳን፤ እግዚአብሔርም ለጌታዬ በጎ ያድርግለት፤ በጎም ታደርግላት ዘንድ ባሪያህን አስብ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጌታዬ የምታዝንበት ምክንያት ወይም የኅሊና ጸጸት አይኖርህም፤ በከንቱ ያፈሰስኸውም ደም ሆነ በገዛ እጅህ የተበቀልኸው የለምና። እግዚአብሔር በጎ ነገር ባደረገልህ ጊዜ እኔን አገልጋይህን ዐስበኝ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታዬ የምታዝንበት ምክንያት ወይም የኅሊና ጸጸት አይኖርብህም፤ ምክንያቱም በከንቱ ያፈሰስከው ደም ወይም በገዛ እጅህ የወሰድከው በቀል የለምና። ስለዚህ ጌታ ለጌታዬ በጎ ነገር ባደረገልህ ጊዜም፥ እኔንም አገልጋይህን አስበኝ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምንም ዐይነት ጸጸት ወይም የኅሊና ወቀሳ አይደርስብህም። ጌታዬ ሆይ፥ ያለ ምክንያት ወይም የበቀል እርምጃ ለመውሰድ ብለህ የገደልከው ሰው የለም፤ ስለዚህ ጌታዬ ሆይ፥ እግዚአብሔር በሚባርክህ ጊዜ እኔንም አትርሳኝ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተ በከንቱ ደም እንዳላፈሰስህ፥ በገዛ እጅህም እንዳልተሳካልህ ይህ ዕንቅፋትና የሕሊና ጸጸት በጌታዬ አይሆንልህም፥ እግዚአብሔርም ለጌታዬ በጎ ባደረገልህ ጊዜ፥ ባሪያህን አስብ። |
ነገር ግን በጎ ነገር በተደረገልህ ጊዜ እኔን ዐስበኝ፤ ምሕረትንም አድርግልኝ፤ ስለ እኔም ለፈርዖን አሳስበህ ከዚህ እስር ቤት አውጣኝ፤
ወንድሞቻችን፥ ራሳችሁ አትበቀሉ፤ ቍጣን አሳልፏት፥ “እኔ እበቀላለሁ፤ እኔ ብድራትን እከፍላለሁ ይላል እግዚአብሔር” ተብሎ ተጽፎአልና።
በእግዚአብሔር ቸርነትና ይቅርታ መመኪያችንና የነፃነታችን ምስክር ይህቺ ናትና፥ በሥጋዊ ጥበብ ሳይሆን፥ በእግዚአብሔር ጸጋ በዚህ ዓለም፥ ይልቁንም በእናንተ ዘንድ ተመላለስን።
አሁንም የእስራኤል ንጉሥ ማንን ለማሳደድ ወጥተሀል? አንተስ ማንን ታሳድዳለህ? የሞተ ውሻን ታሳድዳለህን? ወይስ ቍንጫን ታሳድዳለህ?
እንዲህም ይሆናል፤ እግዚአብሔር ለጌታዬ የተናገረውን ቸርነት ሁሉ ያደርግልሃል፤ በእስራኤልም ላይ አለቃ አድርጎ ይሾምሃል፤
የዳዊትም ብላቴኖች ወደ ቀርሜሎስ ወደ አቤግያ መጡ፥ “ዳዊትም ሚስት ትሆኚው ዘንድ ወደ አንቺ ልኮናል” ብለው ነገሩአት።
ዛሬም እግዚአብሔር በእጄ አሳልፎ ሰጥቶህ ሳለ እግዚአብሔር በቀባው ላይ እጄን እዘረጋ ዘንድ አልወደድሁምና ለሁሉ እያንዳንዱ እግዚአብሔር እንደ ጽድቁና እንደ እምነቱ ፍዳውን ይክፈለው።