1 ሳሙኤል 21:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ካህኑም ለዳዊት መልሶ፥ “ሁሉ የሚበላው እንጀራ የለኝም፤ ነገር ግን የተቀደሰ እንጀራ አለ፤ ብላቴኖቹ ከሴቶች ንጹሓን እንደ ሆኑ መብላት ይችላሉ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ካህኑም ዳዊትን፣ “ሰው ሁሉ የሚበላው እንጀራ የለኝም፤ ነገር ግን ሰዎቹ በቅርቡ ከሴት የተጠበቁ ከሆነ፣ የተቀደሰ እንጀራ በዚህ አለ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ካህኑም፥ “ሰው ሁሉ የሚበላው እንጀራ የለኝም፤ ነገር ግን ሰዎቹ በቅርቡ ከሴት የተጠበቁ ከሆነ፥ የተቀደሰ እንጀራ በዚህ አለ” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ካህኑም “ከተቀደሰው ኅብስት በቀር ሕዝብ የሚመገበው እንጀራ የለኝም፤ ተከታዮችህ በቅርቡ ከሴቶች ጋር ሳይገናኙ ተቈጥበው በንጽሕና የቈዩ ከሆኑ፥ ይህን ኅብስት መብላት ይችላሉ” ሲል መለሰለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ካህኑም ለዳዊት መልሶ፦ ሁሉ የሚበላው እንጀራ የለኝም፥ ነገር ግን የተቀደስ እንጀራ አለ፥ ብላቴኖቹ ከሴቶቹ ንጹሐን እንደ ሆኑ መብላት ይቻላል አለው። |
ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር ቤት ካህናት ለነቢያትም፦ ባለፉት ዓመታት እንዳደረግሁት በአምስተኛው ወር መለየትና ማልቀስ ይገባኛልን? ብለው ይናገሩ ዘንድ ልኮአቸው ነበር።
ለጸሎት እንድትተጉ ከምትስማሙበት ጊዜ ብቻ በቀር፥ ባልና ሚስት አትለያዩ፤ ዳግመኛ ሰይጣን ድል እንዳያደርጋችሁ በአንድነት ኑሩ፤ ሰውነታችሁ ደካማ ነውና ።
ካህኑ አቤሜሌክም በእርሱ ፋንታ ትኩስ እንጀራ ይደረግ ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት ከአለው ኅብስት በቀር ሌላ እንጀራ አልነበረምና የቍርባኑን ኅብስት ሰጠው።