እርሱም ከብላቴኖቹ ጋር በሌሊት ደረሰባቸው፤ መታቸውም፤ በደማስቆ ግራ እስካለችውም እስከ ሖባ ድረስ አሳደዳቸው።
1 ነገሥት 11:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም የሲባን ሰዎች በገደለ ጊዜ ሬዞን ሰዎችን ሰብስቦ የጭፍራ አለቃ ሆነ፤ ወደ ደማስቆም ሄዱ፥ በዚያም ተቀመጡ፤ በደማስቆም ላይ አነገሡት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊት የሱባን ኀይል በደመሰሰ ጊዜ፣ ሬዞን ሰዎቹን በዙሪያው አሰባስቦ የወንበዴ አለቃ ሆነ፤ ሰዎቹም ወደ ደማስቆ ሄደው ተቀመጡ፤ በዚያም አነገሡት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሽፍቶች አለቃ ሆኖ ነበር፤ ይህም የሆነው ዳዊት ሀዳድዔዜርን ድል ነሥቶ የእርሱ ጦር ተባባሪዎች የሆኑትን ሶርያውያንን ከፈጀ በኋላ ነበር፤ ረዞንና ተከታዮቹም ወደ ደማስቆ ሄዱ፤ በዚያም ሲኖሩ እርሱን የሶርያ ንጉሥ እንዲሆን አደረጉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሸፍቶች አለቃ ሆኖ ነበር፤ ይህም የሆነው ዳዊት ሀዳድዔዜርን ድል ነሥቶ የእርሱ ጦር ተባባሪዎች የሆኑትን ሶርያውያንን ከፈጀ በኋላ ነበር፤ ረዞንና ተከታዮቹም ወደ ደማስቆ ሄዱ፤ በዚያም ሲኖሩ እርሱን የሶርያ ንጉሥ እንዲሆን አደረጉት፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም የሱባን ሰዎች በገደለ ጊዜ ሬዞን ሰዎችን ሰብስቦ የጭፍራ አለቃ ሆነ፤ ወደ ደማስቆም ሄዱ፤ በዚያም ተቀመጡ፤ በደማስቆም ላይ አነገሡት። |
እርሱም ከብላቴኖቹ ጋር በሌሊት ደረሰባቸው፤ መታቸውም፤ በደማስቆ ግራ እስካለችውም እስከ ሖባ ድረስ አሳደዳቸው።
ሶርያውያንም ከእስራኤል ፊት ሸሹ፤ ዳዊትም ከሶርያውያን ሰባት መቶ ሰረገለኞችን፥ አርባ ሺህም ፈረሰኞችን ገደለ፤ የሠራዊቱንም አለቃ ሶቤቅን መታ፤ እርሱም በዚያ ሞተ።
የአሞንም ልጆች የዳዊት ወገኖች እንደ አፈሩ ባዩ ጊዜ፥ የአሞን ልጆች ልከው ከቤትሮዖብ ሶርያውያንና ከሱባ ሶርያውያን ሃያ ሺህ እግረኞችን፥ ከአማሌቅ ንጉሥም አንድ ሺህ ሰዎችን፥ ከአስጦብም ዐሥራ ሁለት ሺህ ሰዎችን ቀጠሩ።
የአሞንም ልጆች ወጥተው በበሩ መግቢያ ፊት ለፊት ይዋጉ ጀመሩ፤ የሱባና የሮዖብ ሶርያውያን፥ የአስጦብና የአማሌቅም ሰዎች ለብቻቸው በሰፊ ሜዳ ላይ ነበሩ።
በሰሎሞንም ዘመን ሁሉ የእስራኤል ጠላት ነበረ። አዴርም ያደረጋት ክፋት ይህች ናት፤ እስራኤልን አስጨነቀ በኤዶምያስም ነገሠ።
አሳም በእግዚአብሔር ቤትና በንጉሥ ቤተ መዛግብት የተገኘውን ብርና ወርቅ ሁሉ ወስዶ ለአገልጋዮቹ ሰጣቸው፤ ንጉሡም አሳ በደማስቆ ለተቀመጠው ለአዚን ልጅ ለጤቤርማን ልጅ ለሶርያ ንጉሥ ለወልደ አዴር፥
እግዚአብሔርም አለው፥ “ሂድ፤ በመጣህበትም መንገድ በምድረ በዳ ወደ ደማስቆ ተመለስ፤ ከዚያም በደረስህ ጊዜ በሶርያ ላይ ንጉሥ ይሆን ዘንድ አዛሄልን ቅባው፤
የቀረውም የኢዮርብዓም ነገር፥ ያደረገውም ሁሉ፥ ኀይሉም፥ የይሁዳ የነበረውን ደማስቆንና ሔማትን ለእስራኤል እንደ መለሰ፥ እነሆ፥ በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን?
ኤልሳዕም ወደ ደማስቆ ሄደ፤ የሶርያም ንጉሥ ወልደ አዴር ታምሞ ነበር፤ “የእግዚአብሔር ሰው ወደዚህ መጥቶአል” ብለውም ነገሩት።
ምንአልባት በመንገድ የሚያገኘው ሰው ቢኖር ወንዶችንም ሴቶችንም እያሰረ ወደ ኢየሩሳሌም ያመጣቸው ዘንድ በደማስቆ ላሉት ምኵራቦች የሥልጣን ደብዳቤ ከሊቀ ካህናቱ ለመነ።