1 ነገሥት 11:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)24 የሽፍቶች አለቃ ሆኖ ነበር፤ ይህም የሆነው ዳዊት ሀዳድዔዜርን ድል ነሥቶ የእርሱ ጦር ተባባሪዎች የሆኑትን ሶርያውያንን ከፈጀ በኋላ ነበር፤ ረዞንና ተከታዮቹም ወደ ደማስቆ ሄዱ፤ በዚያም ሲኖሩ እርሱን የሶርያ ንጉሥ እንዲሆን አደረጉት። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም24 ዳዊት የሱባን ኀይል በደመሰሰ ጊዜ፣ ሬዞን ሰዎቹን በዙሪያው አሰባስቦ የወንበዴ አለቃ ሆነ፤ ሰዎቹም ወደ ደማስቆ ሄደው ተቀመጡ፤ በዚያም አነገሡት። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም24 የሸፍቶች አለቃ ሆኖ ነበር፤ ይህም የሆነው ዳዊት ሀዳድዔዜርን ድል ነሥቶ የእርሱ ጦር ተባባሪዎች የሆኑትን ሶርያውያንን ከፈጀ በኋላ ነበር፤ ረዞንና ተከታዮቹም ወደ ደማስቆ ሄዱ፤ በዚያም ሲኖሩ እርሱን የሶርያ ንጉሥ እንዲሆን አደረጉት፤ Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)24 ዳዊትም የሲባን ሰዎች በገደለ ጊዜ ሬዞን ሰዎችን ሰብስቦ የጭፍራ አለቃ ሆነ፤ ወደ ደማስቆም ሄዱ፥ በዚያም ተቀመጡ፤ በደማስቆም ላይ አነገሡት። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)24 ዳዊትም የሱባን ሰዎች በገደለ ጊዜ ሬዞን ሰዎችን ሰብስቦ የጭፍራ አለቃ ሆነ፤ ወደ ደማስቆም ሄዱ፤ በዚያም ተቀመጡ፤ በደማስቆም ላይ አነገሡት። Ver Capítulo |