1 ቆሮንቶስ 9:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እህልህን በምታበራይበት ጊዜ የበሬውን አፉን አትሰረው።” እንግዲህ ይህን የጻፈ ለእግዚአብሔር በሬ አሳዝኖት ነውን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሙሴ ሕግ፣ “የሚያበራየውን በሬ አፉን አትሰር” ተብሎ ተጽፏልና። ለመሆኑ፣ እግዚአብሔርን ያሳሰበው የበሬ ጕዳይ ነውን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የሚያበራየውን በሬ አፉን አትሰር፤” ተብሎ በሙሴ ሕግ ተጽፎአል። እግዚአብሔር ይህን ያለው ስለ በሬዎች በማሰብ ነውን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የሚያበራየውን በሬ አፉን አትሰር” ተብሎ በሕግ ተጽፎአል፤ ታዲያ እግዚአብሔር ይህን ያለው ስለ በሬዎች በማሰብ ነውን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕግስ ደግሞ ያን አይልምን? የሚያበራየውን በሬ አፉን አትሰር ተብሎ በሙሴ ሕግ ተጽፎአልና። እግዚአብሔርስ ስለ በሬዎች ይገደዋልን? |
እኔስ ቀኛቸውንና ግራቸውን የማይለዩ ከመቶ ሃያ ሺህ የሚበልጡ ሰዎችና ብዙ እንስሶች ላሉባት ለታላቂቱ ከተማ ለነነዌ አላዝንምን?” አለው።
ሰባተኛው ቀን ግን ለእግዚአብሔር ለአምላክህ ሰንበት ነው፤ አንተ እንደምታርፍ ሎሌህና ገረድህ ያርፉ ዘንድ፥ አንተ፥ ወንድ ልጅህም፥ ሴት ልጅህም፥ ሎሌህም፥ ገረድህም፥ በሬህም፥ አህያህም፥ ከብትህም ሁሉ፥ በደጆችህም ውስጥ ያለ መጻተኛ በእርሱ ምንም ሥራ አትሥሩ።